1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቡርኪና ፋሶ ወጣቶች እና ቶማስ ሳንካራ

ማክሰኞ፣ ነሐሴ 26 2007

የቡርኪና ፋሶ ወጣቶች ቶማስ ሳንካራ ሃገሪቱን በፕሬዚደንትነት በመሩባቸው አራት ዓመታት ውስጥ ገና አልተወለዱም ነበር። ያም ቢሆን ግን ወጣቱ ትውልድ የአፍሪቃ ቼ ጉቬራ በመባል ይጠሩ ለነበሩት እና እአአ በ1987 ዓም በወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ለተገደሉት የቀድሞ ፕሬዚደንታቸው ቶማስ ሳንካራ ታላቅ አክብሮት ነው ያለው።

https://p.dw.com/p/1GPjU
Thomas Sankara Präsident Burkina Faso Ankunft in Harare 1986
ምስል Getty Images/AFP/A. Joe

[No title]



በመሆኑም፣ አንድ የተማሪዎች ቡድን በአንድ ወቅት እጅግ ተወዳጅ ለነበሩት የቀድሞ ፕሬዚደንት አክብሮታቸውን ለመግለጽ በመዲናይቱ ዋጋዱጉ በስማቸው አንድ ማዕከል ለማቋቋም በአሁኑ ጊዜ ጥረት ጀምረዋል። የዶይቸ ቬለ ካትሪን ጌንስለር የጻፈችው ዘገባ የበርሊኑ ወኪላችን አዘጋጅቶታል።

ይልማ ኃይለሚካኤል


አርያም ተክሌ
ነጋሽ መሃመድ