1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቡድን ሀያ አስረኛ ዓመት

ዓርብ፣ ታኅሣሥ 2 2002

በኢንዱስትሪ የበለፀጉትና ከአዳጊ አገራት የላቀ የኤኮኖሚ ዕምርታ ያስመዘገቡ ሀያ አገራትን ያቀፈው በእንግሊዘኛው ምህፃር G 20 ወይም ቡድን ሀያ የሚባለው ስብስብ ከተመሰረት እነሆ 10 ዓመቱን ደፈነ ።

https://p.dw.com/p/L0EV
የቡድን ሀያ አባል ሀገራት መሪዎችምስል AP

የቡድኑ መስራች ስብሰባ እ.ጎ.አ ታህሳስ 15 እና16 ,1999 ዓም በርሊን ውስጥ ነው የተካሄደው ። የዚህ ስብስብ ዓላማም እ.ጎ.አ በ 1997 በእስያ ከተከሰተው የፋይናንስ ቀውስ በኃላ የዓለም ዓቀፉን የፋይናንስ ስርዓት ማጠናከር ነበር ። ሆኖም ከአንድ አመት በፊት ዓለምን ያዳረሰው የፋይናንስ ቀውስ ሊገታ ቀርቶ ውዝግቡ እየተባባሰ በመምጣቱ የቡድን ሀያን ታሪክ ምፀታዊ ያደርገዋል ። የቡድን ሀያን አስረኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ክላውስ ኡልሪሽ ያቀረበውን ዘገባ ሂሩት መለሰ አጠናቅራዋለች ።

ክላውስ ኡልሪሽ ፣ ሂሩት መለሰ ፣

አርያም ተክሌ