1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቡድን 8 ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጉባኤ ፍፃሜ

ሐሙስ፣ ሚያዝያ 3 2005

የአስተናጋጇ የብሪታኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዊሊያም ሄግ ከጉባኤው ፍፃሜ በኋላ በሰጡት መግለጫ ከ70 ሺህ በላይ የሚገመት ህዝብ እንዳለቀበት ለሚገመተው የሶሪያው ግጭት ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቹ መፍትሄ ማግኘት እንደተሳናቸው አስታውቀዋል ።

https://p.dw.com/p/18EX9
ምስል Reuters


ለንደን ብሪታኒ ውስጥ ለ2 ቀናት የተነጋገሩት የቡድን 8 አባል ሃገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በሶሪያው ግጭት መፍትሄ ፍለጋ ም ሆነ ከሰሜን ኮሪያ በኩል ላለው ስጋት በሚነድፉት እቅድ ላይ ሳይስማሙ ተለያዩ ። የአስተናጋጇ የብሪታኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዊሊያም ሄግ ከጉባኤው ፍፃሜ በኋላ በሰጡት መግለጫ ከ70 ሺህ በላይ የሚገመት ህዝብ እንዳለቀበት ለሚገመተው የሶሪያው ግጭት ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቹ መፍትሄ ማግኘት እንደተሳናቸው አስታውቀዋል ። ሰሜን ኮሪያ የኒዩክልየር የጦር መሣሪያ ማምረቷን የተቃወሙት የቡድኑ አባላት ከፕዮንግያንግ በኩል ላለው ስጋት የሚወስዷቸውን ግልፅ እርምጃዎች ግን አላስቀመጡም ። ስለ ቡድን 8 የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጉባኤየለንደኑን ዘጋቢያችንን ድልነሳ ጌታነህን ጠይቀናል ።
ድልነሳ ጌታነህ
ሂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ