1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቢላል ጋዜጠኞች ፍርድ ቤት አለመቅረባቸዉ

ረቡዕ፣ ነሐሴ 8 2005

ዛሬ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ ተብለዉ የተጠበቁት ቢላል የተሰኘዉ የኢንተርኔት ራዲዮ ሁለት ጋዜጠኞች እስከ ቀኑ አስር ሰዓት ድረስ ወደፍርድ ቤቱ ብቅ እንዳላሉ ተገለጸ።

https://p.dw.com/p/19Q4X
ምስል AP

የራዲዮዉ ከፍተኛ አዘጋጅ ዳርሰማ ሶሪ እና የዜና አዘጋጅ የሆነዉ ኻሊድ መሐመድ ክስ ሳይመሠረትባቸዉ እስር ላይ እንደሚገኙ ለጋዜጠኞች መብት የሚሟገተዉ ዓለም ዓቀፉ ድርጅት CPJ አስታዉቋል። የታሰሩትን ጋዜጠኞች አግኝቶ ማነጋገር እንዳልተቻለ የገለጹልን የህግ ባለሙያና ጠበቃ አቶ ዳዊት ነጋሽ ይቀርቡበታል በተባለዉ ፍርድ ቤት ዛሬ ለረዥም ሰዓታት መጠበቃቸዉን አመልክተዋል። ስቱዲዮ ከመግባቴ አስቀድሜ የሕግ ባለሙያዉን በስልክ አነጋግሬያቸዋለሁ፤

ሸዋዬ ለገሠ

ሂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ