1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ቢል ጌትስ በአዲስ አበባ

ዓርብ፣ ሐምሌ 15 2008

ቢሊየነሩ ቢል ጌትስ የግብርና ምርቶችን በጥራት እና በመጠን ማሳደግ በኢትዮጵያ ከድርቅጋር ለተያያዙ ችግሮች ዘላቂ መፍትሄ መሆኑን አስታወቁ ።

https://p.dw.com/p/1JUPB
Bill Gates Stiftung Runder Tisch Diskussionen im Sheraton Hotel Addis
ምስል DW/G.Tedla

[No title]

በተለያዩ የበጎ አድራጎት ሥራቸው የሚታወቁት የማይክሮሶፍት ባለቤት ቢል ጌትስ አዲስ አበባ ውስጥ ለሃገር ውስጥ እና ለውጭ ጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ በሃገሪቱ ለአረንጓዴ የግብርና ዘዴ ተጨማሪ ድጋፍ ቢሰጥ ፈታኝ ችግሮችን መቋቋም እንደሚቻልም ተናግረዋል ። ርሳቸው እና ባለቤታቸው የመሠረቱት ቢልና ሜሊንዳ ጌትስ የተባለው ድርጅታቸው በኢትዮጵያ ከ500 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር በላይ ካፒታል የሚያንቀሳቀሱ ከ150 የሚበልጡ ፕሮጀክቶች እንዳሉት የሃገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል ።ጋዜጣዊ መግለጫውን የተከታተለው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ዝርዝሩን ልኮልናል ።
ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ