1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የባህረ ሰላጤ ሀገራት ውዝግብ እና የአውሮጳ ህብረት 

ማክሰኞ፣ ሐምሌ 18 2009

ሳውዲ ዐረቢያ፣ የተባበሩት የዐረብ ኤሚሬቶች፣ ባህሬን፣ የመን እና ግብፅ  ከካታር ጋር ዲፕሎማቲክ ግንኙነታቸውን ካቋረጡ እና ማዕቀብ ከጣሉባት  አንድ ወር ከሶስት ሳምንት አልፈዋል። እነዚህ ዐረባውያት ሀገራት ውዝግባቸውን ያበቁ ዘንድ አንዷ የባህረ ሰላጤ ሀገር የሆነችው ኩዌት የሽምግልና ጥረት ጀምራለች።

https://p.dw.com/p/2h7dl
Belgien Federica Mogherini
ምስል picture alliance/dpa/G. Vanden Wijngaert

ዐረባውያት ሀገራት ለአካባቢው ጭምር ስጋት የሆነውን ውዝግባቸውን እንዲያበቁ ሞጌሪኒ ጠየቁ።

ሌሎች ሀገራት እና ተቋማትም ለመሸምገል ሙከራ ይዘዋል። ከነዚህ መካከል አንዱ የሆነውን የአውሮጳ ህብረት በመወከል ወደ ባህረ ሰላጤው ተጉዘው የነበሩት የውጭ ጉዳይ ተጠሪ ፌዴሪካ ሞጌሪኒ  ውዝግቡ ለሚመለከታቸው ብቻ ሳይሆን ለጠቅላላ አካባቢውም አስጊ መሆኑን አስጠነቀቁ።

ገበያው ንጉሤ

አርያም ተክሌ

ነጋሽ መሀመድ