1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የባህር ወንበዴዎችና ሂዝቡል ኢስላም

Mesayረቡዕ፣ ሚያዝያ 27 2002

ሂዝቡል ኢዝላሚያ ያለፈው ሰኞ ሃርዴር የተሰኘችን የባህር ላይ ወንበዴዎች ዋንኛ መሸሸጊያ ከተማ እንደተቆጣጠረ ነበር ፣ ከዚህ በኋላ የባህር ላይ እገታ አይኖርም ያለው።

https://p.dw.com/p/NFBA
እስላማዊ ታጣቂዎች በመቃዲሾምስል AP

ይህ አክራሪ ቡድን ሃርዴርን በእጁ እንዳስገባ የሸሪዓ ህግ ተግባራዊ እንዲሆን አውጇል። ያለምንም የተኩስ ልውውጥ ሃርዴርን የተቆጣጠረው ሂዝቡል፤ ከአልቃኢዳ ጋር ግንኙነት እንዳለው ይታመናል። መሪው ሼክ ዳሂር አዌስ ከእስላማዊው የፍርድ ቤቶች ህብረት መበተን በኋላ ሂዝቡልን ይዘው ዳግም ሶማልያን ለመቆጣጠር እየገሰገሱ ነው። ባለፈው ሰኞ ሃርዴርን ከወንበዴዎች ካስለቀቁ በኋላ የበላይነትን እያገኙ ነው። አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደዘገበው የባህር ላይ ወንበዴዎቹ ለጊዜው ከሃርዴር ሸሽተዋል። በሂዝቡል ድል የሃርዴርም ሆኑ የሞቃዲሾ ነዋሪዎች ደስተኞች እንደሆኑ ተዘግብዋል።

መሳይ መኮንን

ሸዋዩ ለገሠ