1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የባሕር ዳር ዩኒቨርስቲና ተማሪዎች

ረቡዕ፣ ጥር 15 2005

ሙስሊሞች ደቡብ አፍሪቃ እግር ኳስ ሥታዲዮም ድረስ ገብተዉ «ድምፃችን ይሰማ» ማለታቸዉ ተዘግቧል።በዚሕ መሐል የባሕር ዳር ዩኒቨርስቲ አስተዳደር ሙስሊም ተማሪዎች በዩኒቨርስቲዉ ቅጥር ግቢ እንዳሰግዱ በመከልከሉ በሺ የሚቆጠሩ ተማሪዎች፥ ትምሕርት አቋርጠዉ ፤ ዩኒቨርስቲዉን ለቀዉ ወጥተዋል።

https://p.dw.com/p/17QTs
Muslime feiern das Ende des Ramadans im Nationalstadium von Addis Abeba, Äthiopien Copyright: Getachew Tedla/DW, 19.08.2012, Addis Abeba, Äthiopien
ምስል DW/Tedla Getachew

የነብዩ መሐመድ የልደት በዓል (መዉሊድ) ነገ ይከበራል።አብዛኛዉ ኢትዮጵያዊ ሙስሊም የዘንድሮዉን በዓል የሚያከብረዉ በቅይጥ ስሜት ነዉ።የኢትዮጵያ መንግሥት ያሰራቸዉ የመፍትሔ-አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት የፍርድ ሒደት እንደቀጠለ ነዉ።መንግሥት እስረኞቹን እንዲፈታና በሐይማኖት ጉዳይ ጣልቃ እንዳይገባ የሚጠይቁ ኢትዮጵያዉን ሙስሊሞች ደቡብ አፍሪቃ እግር ኳስ ሥታዲዮም ድረስ ገብተዉ «ድምፃችን ይሰማ» ማለታቸዉ ተዘግቧል።በዚሕ መሐል የባሕር ዳር ዩኒቨርስቲ አስተዳደር ሙስሊም ተማሪዎች በዩኒቨርስቲዉ ቅጥር ግቢ እንዳሰግዱ በመከልከሉ በሺ የሚቆጠሩ ተማሪዎች፥ ትምሕርት አቋርጠዉ ፤ ዩኒቨርስቲዉን ለቀዉ ወጥተዋል።የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚ አብሔር ሥለዩኒቨርቲዉ እና ተማሪዎቹ እርምጃ የሚከተለዉን ዘገባ ልኮልናል።

ዮሐንስ ገብረ እግዚ አብሔር

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሠ