1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቤልጂግ ንጉስ ንግግር ያስከተለው ቁጣ

ዓርብ፣ ታኅሣሥ 19 2005

የኤኮኖሚ ቀውስ መጠቀሚያ በማድረግ ጠባብ የፖለቲካ ፍላጎታቸውን ለማሳካት ከሚሞክሩ ፖለቲከኞች ህዝቡ እንዲጠነቀቅ ያስተላለፉት መልዕክት NVA የተባለውን የሃገሪቱን ዋነኛ የፖለቲካ ፓርቲ አስቆጥቷል ።

https://p.dw.com/p/17Aud
In this photo taken on Tuesday, July 19, 2011 and made available on Wednesday, July 20, 2011, Belgium's King Albert II delivers his traditional National Day speech at the Royal Palace in Brussels. Belgium remains deadlocked in political crisis after more than one year without a government. (AP Photo/Bruno Arnold, Pool)
የቤልጂግ ንጉስ ዳግማዊ አልበርትምስል AP

የቤልጂግ ንጉስ ዳግማዊ አልበርት በገና ዋዜማ ለሃገራቸው ህዝብ ያደረጉት ንግግር ማወዛገቡን ቀጥሏል ። ንጉስ በዚህ ንግግራቸው በአሁኑ ሰአት የተፈጠረውን የኤኮኖሚ ቀውስ መጠቀሚያ በማድረግ  ጠባብ የፖለቲካ ፍላጎታቸውን ለማሳካት ከሚሞክሩ ፖለቲከኞች ህዝቡ እንዲጠነቀቅ ያስተላለፉት መልዕክት NVA የተባለውን የሃገሪቱን ዋነኛ የፖለቲካ ፓርቲ አስቆጥቷል ። የደች ቋንቋ ተናጋሪ የሆኑትን ፍላንደሮችን ከቤልጂግ ነፃ ማውጣት የሚፈልገው ይኽው ፓርቲ ንጉሱ ገለልተኛ መሆን ሲገባቸው በቀጥታ በፓርቲው ላይ ያነጣጠረ አስተያየት በመስጠታቸው ቁጣውን አስምቷል ። የንጉሱ አስተያየት የፖለቲካ ተንታኞችም ተችተውታል ። ስለአወዛጋቢው የንጉስ አልበርት ንግግር የብራሰልሱን ዘጋቢያችንን ገበያው ንጉሴን ስቱድዮ ከመግባታችን በፊት  በስልክ አነጋግሬዋለሁ ።
ገበያው ንጉሴ
ሂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ