1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቤርሉስኮኒ ስንብት እና በኢጣሊያ የመንግሥት ምስረታ ጥረት

እሑድ፣ ኅዳር 3 2004

የኢጣሊያ ፕሬዚደንት ጆርጆ ናፖሊታኖ በአገሪቱ የሽግግር መንግሥት ይቋቋም ዘንድ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ንግግር ጀመሩ።

https://p.dw.com/p/RwHc
ስልጣናቸዉን የለቀቁት ጠቅላይ ሚኒስትር ሲልቪዮ ቤርሉስኮኒምስል dapd

ለጠቅላይ ሚኒስትርነት ለመታጨት የላቀ ዕድል ያላቸው ፖለቲከኛ የቀድሞው የአውሮፓ ሕብረት ኮሜሣር ማሪዮ ሞንቲ እንደሆኑ ተነግሯል። የኢጣሊያ የዜና ምንጮች እንደጠቆሙት የኤኮኖሚው ባለሙያ ሞንቲ ሥልጣን በለቀቁት በሢልቪዮ ቤርሉስኮኒ ፓርቲ ውስጥም ቀስ በቀስ ድጋፍ እያገኙ በመሄድ ላይ ናቸው። በሌላ በኩል የሽግግር መንግሥት ማቋቋሙ ካስቸገረ የም/ቤት ምርጫ እንደ አማራጭ መፍትሄ ሆኖ ተግባር ላይ ሊውል እንደሚችልም ለማወቅ ተችሏል። የ 75 ዓመቱ አንጋፋ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤርሉስኮኒ ትናንት የሮማ ፓርላማ በከባድ የመንግሥት ዕዳ በተወጠረችው አገር ላይ የጣለውን የቁጥባና የለውጥ መርህ ከተቀበለ በኋላ ሥልጣን መልቀቃቸውን ማስታወቃቸው አይዘነጋም። ቤርሉስኮኒ በሙስናና በብልግና ድርጊቶች በአገሪቱ በየጊዜው ሲወቀሱና ሲወነጀሉ መቆየታቸው የሚታወቅ ጉዳይ ነው። ዋና ከተማይቱ ሮማ ውስጥ ትናንት አያሌ ሕዝብ አደባባይ በመውጣት በአከራካሪው ባለሥልጣን ስንብት የተሰማውን ደስታ ገልጿል።

Italien / Rom / Berlusconi Rücktritt
ምስል dapd

አዜብ ታደሰ

መስፍን መኮንን