የቤኔዲክት 16 ተኛ የጀርመን ጉብኝት
ሐሙስ፣ መስከረም 11 2004ማስታወቂያ
ጀርመናዊው ቤኔዲክት 16 ተኛ ዛሬ ጠዋት በርሊን እንደገቡ የጀርመን ፕሬዝዳንት ክርስቲያን ቩልፍና የጀርመንዋ መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል በቴግል አውሮፕላን ማረፊያ በመገኘት አቀባበል አድርገውላቸዋል ። ርዕሰ ሊቃነ ጳ̎ጳሳት ቤኔዲክት 16 ተኛ ዛሬ ቀትር ላይ በበርሊኑ የቤል ቭዩ ቤተ መንግሥት እንዲሁም ማምሻውን በጀርመን ፓርላማ ተገኝተዋው ንግግር አድርገዋል ። ስለ ቤኔዲክት አስራ ስድስተኛ የጀርመን ጉብኝት የበርሊኑን ወኪላችንን ይልማ ኃይለ ሚካኤልን ስቱድዮ ከመግባቴ በፊት በስልክ አነጋግሬዋለሁ ። ይልማ ቤኔዲክት 16 ተኛ ጀርመን የመጡበትን ምክንያትና በፓርላማው ያሰሙትን ንግግር ያስቀድማል ።
ይልማ ኃይለ ሚካኤል
ሂሩት መለሰ
ተክሌ የኋላ