1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ረቡዕ፣ ኅዳር 21 2009

ህዳር 29, 2009 ዓ/ም የሚከበረውን 11ኛውን የኢትዮጵያ «የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን» በመባል የሚጠራዉ በዓል ለማስተናገድ ሐረር ሽር ጉድ እያለች ነው።

https://p.dw.com/p/2TX2S
Karte Äthiopien englisch

Nations Right to Self-Gov. In Ethiopia - MP3-Stereo

በሐረሪ ክልል ዋና ከተማ ሐረር ፣ መንገዶችን ማስፋፋት፣ አደራሾችን መገንባት፣ ከየክልሉ የምመጡትን ከ500 በላይ ሰዎችን ለማስተናገድ እና ሌሌሎች መሰረተ ልማቶች በግምት ወደ ሁለት ብሊዮን ብር በላይ መመደቡን በሐረር ፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤት የIT አማካሪ አቶ አብዱልሰላም አብዱሺ ለዶቼ ቬሌ ተናግረዋል ። በአገሪቱ ያሉ ብሔር ፣ ብሔረሰቦች ህዝቦች ራስን በራስ ማስተዳደርን ጨምሮ የተለያዩ መብቶቻቸው በማይከበሩበት በኢትዮጵያ በዓሉ ትርጉም የለውም የሚሉ ወገኖች አሉ። እነዚህ ወገኖች ለዚህ በምሳሌነት የሚያነሱት በኦሮምያ እና በአማራ ክልሎች እንዲሁም በኮንሶ በተነሱት ጥያቄዎች ሰበብ ደረሱ የሚሏቸውን የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ነው። አቶ አብዱሰላም ግን ከዚህ የተለየ አስተያየት ነው ያላቸው።
የደብረማርቆስ ነዋሪ የሆኑት አቶ ጎይቶም ነጋሽም የአቶ አብዱሰላምን አስተያየትን ይጋራሉ።

የአማራ ክልል ተቃዉሞ መነሻ የማንነት ጥያቄ ባለመከበሩ ነዉ ይላሉ ስማቸዉ እንዳይጠቅስ የጠየቁት ሌላ የባህርዳር ነዋሪ ።እኚሁ አስተያየት ሰጭ «በዓሉን ከማክበር በፊት የሰዎች መብት እንዲከበር መደረግ አለብት።

በኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኦሮሚያ ክልል የቡሌ ሆራ ተወካይ አቶ አበራ ቡኖ በህገ መንግስቱ መሠረት የኢትዮጵያ ብሄር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች፣ ኦሮሚያን ጨምሮ «ራሳቸዉን በራሳቸዉ እያስተዳደሩ ነዉ» ብለዋል።

ሆኖም አንድ የምዕራብ ሃራርጌ ዞን የበዴሳ ከተማ ነዋሪ ግን በአቶ አበራ አስተያየት አይስማሙም። የግለሰብም ሆነ የቡድን መብት ተከበሯል የሚባለዉ መሬት ላይ ሳይሆን በወረቀት ላይ ብቻ ነዉ ያለዉ ይላሉ። እንደምክንያትም የሚጠቅሱት፣ «እነሱ የሚሉትና በእዉነት ተደግፎ መሬት ላይ ያለዉ የሰማይና መሬት ርቀት ያህል ነዉ። ምክንያቱም የኦሮሚያ ክልል ራሱን በራሱ እያስተዳደረ ነው የምንል ከሆነ፣ እንዴት ራሱን እያስተዳደረ ነዉ ብሎ መጠየቅ ነዉ። አሮሚያ ራሱን በራሱ ቢያስተዳድር ኑሮ ኮማንድ ፖስትና ብዙ ችግሮችን ኢየፈጠሩ ያሉ ወታደሮች ለምን አስፈለጉ ታድያ?»

በኦሮሚያና በአማራ ክልል የተከሰተዉን ተቃዉሞ ተከትሎ ኮማንድ ፖስት መቋቋሙ ይታወሳል። ኮማንድ ፖስቱም በተደነገገዉ የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ከ11,600 በላይ ሰዎችን ማሰሩን መንግሥት አስታውቋል።

መርጋ ዮናስ

ሕሩት መለሰ