1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የብሩንዲ የመገናኛ ዘዴ ረቂቅ ሕግና ተቃዉሞዉ

ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 15 2005

ለፕሬዝዳት ፔሪ ንኩሩንዚዛ መንግሥት ግን ነባሩ ሕግ ነፃ መገናኛ ዘዴና ጋዜጠኞችን ለመቆጣጠር «የልብ አድርስ» አይነት አልሆነም።ያ-ሕግ፥ በመንግሥት መግለጫ እንዲሻሻል፥ በጋዜጠኞቹና በጋዜጠኞች መብት ተሟጋቾቹ አይን እንዲጠናከር፥ መወሰኑ ነዉ ያዲሱ ተቃዉሞ ምክንያት

https://p.dw.com/p/18LRk
Burundian journalists carry a banner as they march in the streets of Burundi's capital Bujumbura on May 03, 2011. Hundreds of journalist joined the march to mark the International day of the freedom of the press and called for the release of a fellow journalist, Jean-Claude Kavumbagu, who was arrested by the Burundian authorities and accused of treason for having doubted the Burundian governments ability to prevent a somali Islamist insurgents attack on Burundian soil. The prosecutor in the case is asking for life imprisonment as punishment for the journalist's offense. Burundi is one of the two countries who have provided soldiers to the African Union's military force helping to uphold the Somali transitional government. AFP PHOTO/ESDRAS NDIKUMANA (Photo credit should read Esdras Ndikumana/AFP/Getty Images)
የተቃዉሞ ሠልፍምስል Esdras Ndikumana/AFP/Getty Images

23 04 13

የብሩንዲ መንግሥት አዲስ ያሻሻለዉን የመገኛ ዘዴዎች ሕግ የሐገሪቱ ሕግ መወሰኛ ምክር ቤትና ፕሬዝዳት እንዳያፀድቁት ዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት ድንበር የለሽ ዘጋቢዎች ጠየቀ።መንበሩን ፓሪስ-ፈረንሳይ ያደረገዉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት እንደሚለዉ ሕጉ የገለልተኛ መገናኛ ዘዴዎች ነፃነትን፥ የጋዜጠኞች ሥራና መብትን የሚገድብ ነዉ።የብሩንዲ ሕግ መምሪያ ምክር ቤት በቅርቡ በአብላጫ ድምፅ የተቀበለዉ የማሻሻያ ሕግ በነፃ ጋዜጠኞች ሥራና አሠራር ጥብቅ ቁጥጥር እንዲደረግና ከፍተኛ ቅጣት እንዲጣል የሚደነግግ ነዉ።የብሩንዲ ጋዜጠኞች ማሕበር ሕጉን ነፃ መገናኛ ዘዴዎችን ለመዝጋት ያለመ በማለት አዉግዞታል።ነጋሽ መሐመድ አጭር ዘገባ አለዉ።


የብሩንዲ ነፃ ጋዜጠኞች የእስካሁን ትችት፥ ጥያቄ፥ አንዴዴም ተቃዉሞ፥ የሐገሪቱ መንግሥት እንደ ጎርጎሮሳዉያኑ አቆጣጠር 2003 የደነገገዉ ሕግ፥ መብት-ነፃነታችንን ገደበብን የሚል ነበር።የራዲዮ ዘገቢ ሐሰን ሩቫኩኪ በጤና መታወክ ሰበብ በቅርቡ እስኪለቀቅ ድረስ ለአሥራ-አምስት ወራት ያሕል መታሠሩ የብሩንዲ ጋዜጠኞችና የጋዜጠኞች መብት ተሟጋቾች ነባሩን ሕግ እና መንግሥት ሕጉን አሳቦ የሚወስደዉን እርምጃ ለመተቸት እና ለመቃዋማቸዉ የቅርብ ዋቢ ያደርጉታል።

ለፕሬዝዳት ፔሪ ንኩሩንዚዛ መንግሥት ግን ነባሩ ሕግ ነፃ መገናኛ ዘዴና ጋዜጠኞችን ለመቆጣጠር «የልብ አድርስ» አይነት አልሆነም።ያ-ሕግ፥ በመንግሥት መግለጫ እንዲሻሻል፥ በጋዜጠኞቹና በጋዜጠኞች መብት ተሟጋቾቹ አይን እንዲጠናከር፥ መወሰኑ ነዉ ያዲሱ ተቃዉሞ ምክንያት። በድንበር የለሽ ዘጋቢዎች የአፍሪቃ ጉዳይ ተጠሪ ፔሪ አምብሮይዝ፥-
                    

«የጋዜጠኞችን የመርመር፥ የመናገር፥ የማሳተም ነፃነትን በተመለከተ ካለፈዉ ይልቅ ያሁኑ ሕግ በጣም ያጠበዋል።ምክንያቱም ይሕ ረቂቅ ጋዜጠኞች በጣም በተዘረዘሩ ሰፊ ጉዳዮች ጥፋተኛ ሆነዉ ከተገኙ እጅግ ከፍተኛ መቀጮ ይጣልባቸዋል።ጋዜጠኞች መመርመርና መዘገብ የሚችሉበትን ርዕሥም ይቀንሰዋል።»

በአዲሱ ሕግ መሠረት ጋዜጠኞች ምንጮቻቸዉን በሚስጥር የመያዝ መብት የላቸዉም።አንድ ግለሰብ ያሻዉን ያሕል ልምድ ቢኖረዉም የዩኒቨርስቲ ዲግሪ ከሌለዉ ጋዜጠኛ መሆን አይችልም።ጋዜጠኛዉ የመንግሥትን ሚስጥር፥ የጦር ሐይሉን ሚንስጥር የሚጋልጡ፥ የሕዝብን ጥቅምና ፀጥታ፥  የሚያዉኩ ዘገቦችን አዉጥቷል ወይም ሊያወጣ ሞክሯል ከተባለ ከባድ ቅጣት ይበይነበታል።

እስካሁን ባለዉ ሕግ አንድ መቶ ሐምሳ ዩሮ ግድም የሚያስቀጣዉ ጥፋት አሁን ወደ አንድ ሺሕ ዩሮ ከፍ ብሏል።ጥፋቱ መንግሥት ከባድ ነዉ ብሎ ካሰበ ጋዜጠኛዉ በገንዘብ መቀጫ አያመልጥም።ሊታሰር፥ ጣቢያዉ ወይም ጋዜጣዉ ሊዘጋም ይችላል።

ጋዜጠኛዉን ያስከስሳሉ የተባሉት የሕዝብ፥ የመንግሥትና የመከላከያ ደሕንነት ፀጥታና ሚስጥር ግን በግልፅ አልተቀመጡም።የብሩንዲ የጋዜጠኞች ማሕበር ፕሬዝዳት አሌክሳንደር ኒዩንጌኮ ሕጉን «ነፃ መገናኛ ዘዴዎችን ለመዝጋት ያለመ» በማለት አዉግዘዉታል።የድንበር የለሽ ዘጋቢዎች ባለሥልጣን አብሮይዝ እንደሚሉት ደግሞ፥ አሻሚ እና ለዲሞክራሲያዊ ሥርዓት አደገኛ ነዉ።
                     
«ይሕ በጣም አሻሚ፥ ግን በጣም ጨካኝ ሕግ ነዉ።ጋዜጠኞች ጥንቃቄ የሚያሻቸዉ የሚባሉ ጉዳዮችን ለማጣራት፥ ለመርመርና ለመዘገብ ከሞከሩ የሚጣልባቸዉ ቅጣት እጅግ ከባድ ነዉ። ተቃዋሚዎች አቋማቸዉን በግልፅ መግለፅ በማይችሉባት ብሩንዲን በመሰለች ሐገር መገናኛ ዘዴዉ ሥራዉን መስራት ካልቻለ፥ የሚሰማዉ ድምፅ የገዢዉ ፓርቲ «የገደል ማሚቶ» ብቻ ነዉ።በዚሕም ምክንያት የኛ ሥጋት ለፕሬስ ነፃነት ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ለአደጋ የተጋለጠ በመሆኑ ነዉ።»


ማሻሻያዉን የሐገሪቱ ሕግ መምሪያ ምክር ቤት በአብላጫ ድምፅ ተቀብሎታል።ሕግ የሚሆነዉ ግን የሐገሪቱ ሕግ መወሰኛ ምክር ቤት አፅድቆት፥ በፕሬዝዳንቱ ፊርማ ሲፀና ነዉ።ብሩንዱ በያዝነዉ የጎርጎሮሳዉያን ዓመት ሁለት ሺሕ አስራ-ሰወስት የፕረስ ነፃነትን በማክበር ከአንድ መቶ ሰባ ዘጠኝ ሐገራት አንድ መቶ ሠላሳ-ሁለተኛ ናት።

ነጋሽ መሐመድ

Burundian journalists march in the streets of Burundi's capital Bujumbura on May 03, 2011. Hundreds of journalist joined the march to mark the International day of the freedom of the press and called for the release of a fellow journalist, Jean-Claude Kavumbagu, who was arrested by the Burundian authorities and accused of treason for having doubted the Burundian governments ability to prevent a Somali Islamist insurgents attack on Burundian soil. The prosecutor in the case is asking for life imprisonment as punishment for the journalist's offense. Burundi is one of the two countries who have provided soldiers to the African Union's military force helping to uphold the Somali transitional government. Slogan translates as 'Freedom of the Press. Where are we? Where are we going?' AFP PHOTO/ESDRAS NDIKUMANA (Photo credit should read Esdras Ndikumana/AFP/Getty Images)
ቡሩንዲ የፕረስ ነጻነትምስል Esdras Ndikumana/AFP/Getty Images
An activist of Reporters Without Borders (Reporters Sans Frontieres- RSF) takes part in a protest in front of an Iran Air agency in Paris, on July 10, 2012 to denounce journalists' imprisonment in Iran and to commemorate the 10th anniversary of the death in jail of Iranian photo-reporter Zahra Kazemi. AFP PHOTO / LOIC VENANCE (Photo credit should read LOIC VENANCE/AFP/GettyImages)
የፕረስ ነጻነትምስል Loic Venance/AFP/GettyImages
ARCHIV - Die Präsidentenwahlen im ostafrikanischen Kleinstaat Burundi am 28. Juni 2010 sollten Demokratisierung und Friedensprozess nach mehr als zehnjährigem Bürgerkrieg festigen. Statt dessen überschatten Misstrauen, Manipulationsvorwürfe und der Rückzug aller Oppositionskandidaten den Urnengang. Amtsinhaber Pierre Nkurunziza (Archivfoto vom 17.11.206) , ein ehemaliger Rebellenführer, tritt wie schon im Jahr 2005 als einziger Kandidat für eine weitere fünfjährige Amtszeit an. Zuletzt zog selbst Yves Sahinguvu vom Koalitionspartner Uprona, seine Kandidatur um das Präsidentenamt zurück. Foto : OLIVIER HOSLET (zu dpa-Korr "Präsidentenwahlen in Burundi von Boykott überschattet" vom 21.06.2010) +++(c) dpa - Bildfunk+++
ፕሬዝዳንት ንኩሩንዚዛምስል picture alliance/dpa

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ