1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የብሩንዲ የማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፐብሊክና የማሊ ቀውስ

ቅዳሜ፣ ታኅሣሥ 30 2008

መንግሥት የአፍሪቃ ህብረት ሰላም አስከባሪ ኃይል ወደ ብሩንዲ እንዲላክ ህብረቱ ያሳለፈውን ውሳኔ ከመቃወም አልፎ ወታደሮች ከመጡ እወጋቸዋለሁ ማለቱም ማነጋገሩ ቀጥሏል ። ኡጋንዳ የብሩንዲ መንግሥት እወስዳለሁ ያለው ይህ እርምጃ ስህተት ነው ስትል ትናንት አስታውቃለች ።

https://p.dw.com/p/1HalJ
Burundi Gewalt und Tote
ምስል picture-alliance/AP Photo

የብሩንዲ የማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፐብሊክና የማሊ ቀውስ

የብሩንዲ ቀውስ ከዕለት ወደ እለት እየተባባሰ ሄዷል ። በብሩንዲ ሰላም ለማውረድ ባለፈው ሰሞን የተሞከረው የሰላም ንግግርም እንደታሰበው መቀጠሉ አጠራጣሪ ሆኗል ። ከብሩንዲ አማፅያን ቡድኖች አንዳንዶቹ ከመንግሥት ጋር የመነጋገር ፍላጎት እንደሌላቸው ከወዲሁ እያሳወቁ ነው ። መንግሥትም በሃገሪቱ ፕሬዝዳንት ፕየር ንኩሩንዚዛ ላይ መፈንቅለ መንግሥት ያሴሩ ቡድኖች በንግግሩ መካተት የለባቸውም ሲል በኢንቴቤው የሰላም ንግግር ላይ አልተገኘም ። የተባበረ ኃይል መሥርተናል የሚለው አንድ የአማፅያን ቡድን ፕሬዝዳንት ንኩሩንዚዛን ከሥልጣን ለማውረድ እየዛተ ነው። መንግሥት የአፍሪቃ ህብረት ሰላም አስከባሪ ኃይል ወደ ብሩንዲ እንዲላክ ህብረቱ ያሳለፈውን ውሳኔ ከመቃወም አልፎ ወታደሮች ከመጡ እወጋቸዋለሁ ማለቱም ማነጋገሩ ቀጥሏል ። ኡጋንዳ የብሩንዲ መንግሥት እወስዳለሁ ያለው ይህ እርምጃ ስህተት ነው ስትል ትናንት አስታውቃለች ።ብሩንዲ የህብረቱን ሰላም አስከባሪ ኃይል እንድትቀበል የተሰጣት ቀነ ገደብ አልፏል ። የዛሬው ትኩረት በአፍሪቃ ማብቂያ ባልተገኘለት የብሩንዲ ቀውስ በማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፐብሊክና በማሊ የፀጥታ ችግር ላይ ያተኩራል ። ለቅንብሩ ገበያው ንጉሴ