1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የብሪታኒያ ካሳ ለቀድሞ የዋንታናሞ ዕስረኞች

ረቡዕ፣ ኅዳር 8 2003

የብሪታኒያ መንግስት ለቀድሞ የዋንታሞ ዕስረኞች ካሳ ለመክፈል መወሰኑን ትናንት አስታውቋል ። መንግስት እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰውም በእስር ላይ ሳሉ በደል ደርሶብናል ሲሊ ከከሰሱ የቀድሞ እስረኞች ጠበቆች ጋር ለሳምንታት ከተካሄደ ድርድር በኃላ ነው ።

https://p.dw.com/p/QBTD
ብንያም ሞሀመድምስል AP

ከፍርድ ቤት ውጭ በተካሄደ በዚሁ ስምምነት መሰረት መንግስት ለተበዳዮቹ ከ1 ሚሊዮን ፓውንድ ወይም ከ 1.6 ሚሊዮን ዶላር በላይ ካሳ ይከፍላል ። ከፍተኛው ካሳ ከሚያገኙት ከሳሾች ውስጥ የብሪታኒያው ነዋሪ ኢትዮጵያዊው ብንያም ሞሀመድ አንዱ መሆኑን የለንደኑ ወኪላችን ድልነሳ ጌታነህ ዘግቧል ።

ድልነሳ ጌታነህ ፣ ሂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሠ