1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የብሪታንያዋ እንደራሴ ግድያ

ዓርብ፣ ሰኔ 10 2008

የ41 ዓመቷን የሠራተኛ ወይም ሌበር ፓርቲን እንደራሴ በሰወስት ጥይት ደብድቦ እና በጩቤ ጨቅጭቆ ገድሏል የተባለ አንድ የ52 ዓመት ጎልማሳ ታስሯል።ታዛቢዎች እንደሚሉት ወይዘሮ ኮክስ፤ ብሪታንያ ከአዉሮጳ ሕብረት አባልነት ትዉጣ-አትዉጣ የሚለዉ የተካረረ ዉዝግብ ሰለባ ናቸዉ

https://p.dw.com/p/1J8tW
ምስል Reuters/Press Association/Y. Mok

[No title]

የብሪታንያ ፖለቲከኞች ትናንት ሰሜናዊ ኢንግላንድ ዉስጥ በጥይት ተደብድበዉ በተገደሉት በሐገሪቱ የምክር ቤት ባልደረባ በወይዘሮ ጆ ኮክስ ሞት የተሰማቸዉን ሐዘን እየገለጡ ነዉ።የ41 ዓመቷን የሠራተኛ ወይም ሌበር ፓርቲን እንደራሴ በሰወስት ጥይት ደብድቦ እና በጩቤ ጨቅጭቆ ገድሏል የተባለ አንድ የ52 ዓመት ጎልማሳ ታስሯል።ታዛቢዎች እንደሚሉት ወይዘሮ ኮክስ፤ ብሪታንያ ከአዉሮጳ ሕብረት አባልነት ትዉጣ-አትዉጣ የሚለዉ የተካረረ ዉዝግብ ሰለባ ናቸዉ።ሟቿ ብሪታንያ የአዉሮጳ ሕብረት አባል እንደሆነች መቀጠል አለባት የሚል አቋም አራማጅ ነበረ። ፖሊስ ዛሬ እንዳስታወቀዉ በገዳይነት የተጠረጠረዉ ግለሠብ ቀልቡን የሳተ ወፈፌ ብጤ ነዉ።የለንደኑ ወኪላችን ድልነሳ ጌታነሕ ዝርዝር ዘገባ አለዉ።

ድልነሳ ጌታነሕ

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሰ