የብሪታንያ ምርጫ ፣ የመንግስት ምስረታ ውጣ ውረድ እና አስተምህሮቱ
ማክሰኞ፣ ግንቦት 3 2002ማስታወቂያ
በሐሙሱ ምርጫ የወግ አጥባቂዎቹ ፓርቲ አብላጫውን የምክር ቤት መቀመጫ አግኝቷል ። ገዥው የሌበር ወይም የሰራተኛ ፓርቲ ደግሞ ሁለተኛውን ደረጃ ሲይዝ ፣ የሊብራል ዲሞክራቶች ወይም የነፃ ዲሞክራቶች ፓርቲ ሶሶተኛውን ስፍራ አግኝቷል ። ምንም እንኳን ወግ አጥባቂው ፓርቲ ከፍተኛውን የምክር ቤት መቀመጫ ቢያገኝም ለገዥነት የሚያበቃውን ቁጥር አለማሟላቱ ለብቻው መንግስት እንዳይመሰረት መሰረታዊ ዕንቅፋት ሆኖበታል ። ታዲያ ከአሁን በኃላ ብሪታኒያ በማን ትመራ ይሆን ? በአሁኑ መንግስት ምስረታ ወሳኙን ድርሻ የያዘው ፣ የነፃ ዲሞክራቶቹ ፓርቲ ከየትኛው ፓርቲ ጋር ለመጣመር ይስማማ ይሆን ? የዛሬው አውሮፓ እና ጀርመን ዝግጅታችን የብሪታንያ ምርጫ ውጤትና የመንግስት ምስረታውን ውጣ ውረድ እንዲሁም አስተምሆሮቱን ይመለከታል ።
ሂሩት መለሰ
ተክሌ የኋላ