1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የብሪታንያ ከአዉሮጳ ኅብረት መዉጣት

ዓርብ፣ ሰኔ 17 2008

የብሪታንያ ሕዝብ ትናንት በሰጠዉ ድምፅ ሃገሩ ከአዉሮጳ ሕብረት አባልነት እንድትወጣ መወሰኑ የብሪታንያንም ሆነ የኅብረቱን የወደፊት ፖለቲካዊ-ምጣኔ ሐብታዊ ጉዞ መንታ መንገድ ላይ ያቆመዉ መዉስሏል። ብሪታንያ ከአዉሮጳ ሕብረት መዉጣትዋን የሚደግፉት ወገኖች ዉሳኔዉ የብሪታንያን ልዑላዊነትና ነፃነት የሚያረጋግጥ ነዉ በማለት እያወደሱት ነዉ።

https://p.dw.com/p/1JDJT
Brexit David Cameron Presse London
ምስል picture-alliance/dpa/A. Rain

[No title]

ብዙ የፖለቲካ ተንታኞች ግን ዉሳኔዉ ለሁሉም ወገን እንደ ኪሳራ የሚታይ ነዉ ይላሉ።

ውጤቱ ማንንም አይጠቅምም፡፡ ረጋ ብሎ ለሚመለከት ሰው ይህ ውጤት ሁሉም ወገን ምንም ሳያትርፈበት ባዶ እጁን የወጣበት ቀን ነው፡፡„ አዉሮጳን ለቀን እንውጣ!“ ብለው በአለፉት ወራት የተንቀሳቀሱት ወገኖች ድል ያገኙበት ፣ድልም የመቱበት ቀን ሊመስላቸው ይችላል፡፡ግን ! ትንሽ ቆይተው እንደሚረዱት«ይህን ደግሞ በቅርቡ ይረዱታል»ድል እነሱ የተጎናጸፉበት ቀን ሳይሆን ዛሬ ለጥፋት በር የቀደዱበት ቀን ነው፡፡

ዪናይትድ ኪንግደም «ታላቁዋ ብርታኒያ»በዚህ ! እራሱዋ በጀመረችው ጉዞ ነገ ተበታትናም ልትጠፋም ትችላለች፡፡ ስኮትላንድ የተባለው አንደኛው ክፍለአገርንግምት ውስጥ አስገብቶ አሁን በደንብ መመልከት ያስፈልጋል።የአዉሮጳን ማኅበረሰብ፣እንደ እንግሊዞቹ ለቆ ከዚያ ኅብረተሰብ ኑዋሪው ሕዝብ ለመውጣት አይፈልግም፡፡

አየርላንድም እንደዚሁ የኅብረቱ አባል ሁና ለመቆየት ትፈልጋለች፡፡ ይህ ከሆነ ደግሞ ስኮትላንድና አየር ላንድ ከብርታኒያ እንገንጠል የሚለውን የቆየጥያቄአቸውን እንደገና መልስው የሚያነሱበት ቀን ከእንግዲህ እሩቅ አይደለም፡፡ የታላቁዋ ብርታኒያ«ከአዉሮጳ አንድነት መሰናበት»ሌላም ችግር ለቀሩትም መንግሥታት በእርግጠኛነት ይዞም ይመጣል፡፡

እሱም በዓለም አቀፉ የፖለቲካ መድረክ ላይ ማኅበረሰቡ አንድ ላይ ሁኖ በጋራ ያራምደው የነበረው የውጭ ፖሊሲውና የዲፕሎማቲክ ግንኙነቱ እንዲሁም በወታደራዊመስኩ እስከ አሁን ድረስ ይታዩ የነበሩት የጋራ አካሄዶች ወደፊት ሌላ መልክ መያዛቸው የማይቀርለት ነው፡፡በተለይ የብርታኒያ መሰናበት ለጀርመን ፓለቲካ - ከብዙ አቅጣጫ ሲታይ- መጥፎ ነው፡፡ትልቅ ወዳጅዋን ጀርመን በዛሬው ቀን አጥታለች፡፡ቀጣዩ ችግር ደግሞ ከእንግዲህ ሌሎች መንግሥታት ይህን የብርታኒያ ፈለግ ተከትለው እንደይነሱ እነሱን ማገዱ ነው፡፡ ለዚህም ትልቅ አተኩሮ መስጠት ይገባል፡፡

ይህ ከአልተደረገ «ይህም ከአልታሰበበት»ብዙ አገሮች ነገ ተነስተው „ ለመቆየት ሆነ ማኅበረሰቡን ጥሎ ለመውጣት «እኛም»እንደ ብርታኒያ ድምጽ እንስጥበት፣ ይህም ይፈቀድልን “ ብለው እነሱም ሊነሱ ይችላሉ፡፡ ወይም ደግሞ ቀደም ሲል ለብርታኒያ እንደተደረገው „ ለእኛም በአባልነት ለመቆየት ልዩ ድጎማ ከማኅበረሰቡ ይቆረጥልን“ ብለው ጥያቄአቸውን ሠንዝረው ኅብረቱን አንድ ቀን ሊያናጉትም ይችላሉ፡፡

ይህ ከሆነ ደግሞ ፣በስንት መከራ የተገናበው የአዉሮጳ አንድነት ማኅበረሰብ፣በቀላሉ ተዳክሞ በዓለም አቀፉ የፖለቲካ መድረክ ላይ ወደፊት ሊጫወት የሚገባው ሚና፣ ውስን ይሆናል፡፡ ይህ አስፈላጊ አይደለም፡፡ ብርታኒያ በገዛ ፈቃዱዋ፣በገዛ እጅዋ ከማኅበረሰቡ ተሰናብታለች፡፡

ስለዚህ ምንም ማድረግ አይቻልም!ይልቅስ! አሁን ሌሎቹ የተቀሩት ተናደው ቂም በቀሉን ማሰቡን ትተው ከብርታኒያ ጋር ወደፊት አብሮ በጋራ መሥራት የሚቻለውን ነገር ረጋ ብለው አስበውበት አዲስ ፖለቲካ መቀየሱ ላይ ማተኮር ይገባቸዋል፡፡

የአዉሮጳ ማኅበረሰብም በበኩሉ ኅብረቱም እሰከ ዛሬ ድረስ የሠራውንና የወሰደውን እርምጃም መለስ ብሎ መገምገምም ይኖርበታል፡፡ በቂ አወዛጋቢ ሰነዶች አሉ፡፡የስደተኞች ጉዳይ አንደኛው ነው፡፡ ስለ ሓብታምና ደሃ አባል አገሮችም ስለ እነሱም ግኑኝነት - በማኅበረሰቡ ውስጥ የሚታየው አለመግባባት እና አለመደማመጥ እንደገና ተመልሶም መርመርም ይገበዋል፡፡ አላማችን ለጦርነት ቀዳዳ የማይሰጥ „ የሰላም ፕሮጄክት ነው“ በየጊዜው ማለት፣እሱ ብቻውን - ሌሎች ነገሮችን ረስቶ ይህን ማንሳቱ ብቻ በቂ አይደለም፡፡

ታላቁዋ ብርታኒያ ማኅበረሰቡን ጥላ ለመውጣት ያደረገችው እርምጃ ለማንም ሰው በአሁኑ ዘመን አሳዛኝ ነው፡፡ ይህ ግልጽ ነው!ግን ደግሞ እነሱ የወሰዱትን እርምጃ - ለእነሱም ባይጠቅም፣ እላይ እንደተባለው፣ ሊበታተኑም ይችላሉ - ሰው ሁሉ ከተኛበት አልጋው ላይ ተነስቶ እንዲያስብበት የደወሉት ደወል መሆኑን እኛ መርሣት የለብንም፡፡

ጊዜው አሁን ነገሮችን አፍርጦ አለአንዳች መሸፋፈን እነሱን አገላብጦ መመልከትና መገንዘብ ፣ከዚያም ተነስቶ አዳዲስ መፍትሔዎችን ፣ለመጪው አስቸጋሪ ጊዜያቶች የምንነድፍበት ሰዓት ነው፡፡ ችግርም ሲመጣ የሚፈታው በዚህ ዘዴ ነው፡፡


ክርስቶፍ ሃስልባህ / ይልማ ኃይለ ሚካኤል


አዜብ ታደሰ

London Brexit Referendum Symbolbild
ምስል Reuters/R. Krause
Christoph Hasselbach
ክርስቶፍ ሃስልባህምስል DW/M.Müller