1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የብሪክዚት ድርድር

ሐሙስ፣ ሐምሌ 13 2009

የዚህ ሳምንቱ ዋና ድርድር የተጀመረው እና የተካሄደውም ሁለቱ ወገኖች ከአንድ ወር በፊት በተስማሙበት የቅድመ ድርድር እና የአጀንዳ ዝግጅት መሠረት ነው።

https://p.dw.com/p/2gu9K
Belgien - Brexit-Verhandlungen mit Barnier und Davis in Brüssel
ምስል Reuters/F. Lenoir

M M T/ Ber. Brüssel(Brexit talks) - MP3-Stereo

 
ካለፈው ሰኞ ጀምሮ ብራሰልስ ቤልጅየም ውስጥ ሲካሄድ የቆየው የብሪታንያ ከአውሮጳ ህብረት የመውጣት ድርድር ሁለተኛ ዙር ውይይት ዛሬ ተጠናቋል። የዚህ ሳምንቱ ዋና ድርድር የተጀመረው እና የተካሄደውም ሁለቱ ወገኖች ከአንድ ወር በፊት በተስማሙበት የቅድመ ድርድር እና የአጀንዳ ዝግጅት መሠረት ነው። የድርድር መርሃ ግብሩ የሚካሄደው በሁለቱ ወገኖች ስምምነት መሠረት በየወሩ ለ4 ቀናት ነው። ዛሬ ስለተጠናቀቀው ሁለተኛ ዙር የብሪክዚት ድርድር የብራሰልሱ ዘጋቢያችን ገበያው ንጉሴ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል። 
ገበያው ንጉሴ
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ