1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የብራስልሱ ጥቃትና የምዕራባዉያን ሥልት

ዓርብ፣ መጋቢት 16 2008

በቤልጂግ ባለሥልጣናት ላይ የሚሠነዘረዉ ወቀሳና ትችት ግን እንደቀጠለ ነዉ።የአዉሮጳ ሕብረትና የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣናት አሸባሪነትን ለመዋጋት በጋራ እንደሚጥሩ በድጋሚ ቃል እየገቡ ነዉ።ይሁንና ለፀረ-ሽብር ትግሉ አዲስ ሥልት የመቀየስ ዝንባሌ ጨርሶ አላሳዩም።

https://p.dw.com/p/1IK1W
ምስል Getty Images/AFP/P. Huguen

[No title]

የቤልጅግ ባለሥልጣናት ባለፈዉ ማክሰኞ ብራስልን ካሸበሩት ሐይላት ጋር ግንኙነት አላቸዉ ብለዉ የጠረጠሯቸዉን ሰባት ሰዎች መያዛቸዉን አስታዉቀዋል።ጀርመን ዉስጥም ሁለት ተጠርጣሪዎች መያዛቸዉ ሲነገር፤ ፈረንሳይ አደጋ ለመጣል የተወጠነ ሴራ ማክሸፏን አስታዉቃለች።በቤልጂግ ባለሥልጣናት ላይ የሚሠነዘረዉ ወቀሳና ትችት ግን እንደቀጠለ ነዉ።የአዉሮጳ ሕብረትና የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣናት አሸባሪነትን ለመዋጋት በጋራ እንደሚጥሩ በድጋሚ ቃል እየገቡ ነዉ።ይሁንና ለፀረ-ሽብር ትግሉ አዲስ ሥልት የመቀየስ ዝንባሌ ጨርሶ አላሳዩም።የብራስልስ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሴን በስልክ አነጋግሬዉ ነበር።

ገበያዉ ንጉሴን

ነጋሽ መሐመድ

ሒሩት መለሠ