1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የብራና መፅሐፍት ተያዙ

ረቡዕ፣ ጥቅምት 1 2010

ሰዎቹ የተያዙት አንድ መቶ ያክል ታሪካዊ የብራና መፅሐፍትን ወደ ዉጪ ለማስወጣት ሲሞክሩ ቦሌ ዓለም አቀፍ አዉሮፕላን ጣቢያ ነዉ

https://p.dw.com/p/2leYu
Vatikan Archiv
ምስል Megan Williams

(Beri.AA) Parchment books seized in AA - MP3-Stereo

የተለያዩ የብራና መፅሐፍትን ከኢትዮጵያ ለማስወጣት የሞከሩ አንድ ቻይናዊ እና ተባባሪዎቹ ተይዘዉ በፍርድ ቤት መቀጣታቸዉን የኢትዮጵያ የቅርስ ጥናት ጥበቃ ባለሥልጣን አስታወቀ።ሰዎቹ የተያዙት አንድ መቶ ያክል ታሪካዊ የብራና መፅሐፍትን ወደ ዉጪ ለማስወጣት ሲሞክሩ ቦሌ ዓለም አቀፍ አዉሮፕላን ጣቢያ ነዉ።የተያዙት መፅሐፍት ለባለሥልጣኑ ተሰጥተዋል።ይሁንና በሰዎቹ ላይ ሥለተጣለዉ ቅጣትም ሆነ ሥለተያዙበት ቀን የአዲስ አበባዉ ወኪላችን የጌታቸዉ ተድላ ሐይለ ጊዮርጊስ ዘገባ የጠቀሰዉ ነገር የለም።

ጌታቸዉ ተድላ ሐይለ ጊዮርጊስ

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሰ