(Beri.AA) Ethio.Birr Devaluation - MP3-Stereo
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የብር ምንዛሪ ዋጋን መቀነሱ የዋጋ ግሽበትን እንደሚያስከትል አንድ የምጣኔ ሐብት ባለሙያ አስታወቁ።የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ያነጋገራቸዉ ባለሙያ እንደሚሉት የብር ዋጋ መቀነስ ላጭር ጊዜ እፎይታ መጥቀሙ አይቀርም።በረጅም ጊዜ ግን የሸቀጦች ዋጋ ንረትን እና የኑሮ ዉድነትን ያስከትላል።የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንድ የብር የምንዛሪ ዋጋን በ15 ከመቶ ቀንሷል።