1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የብዝሃ ህይወት ጥበቃና ድህነት

ማክሰኞ፣ ግንቦት 5 2000

ተፈጥሮ ለሰዉ ልጆች የተለያዩ ፀጋዎችን ለግሳለች። ያንን ፀጋ በአግባቡ መጠቀም እየቀረ ያለገደብ ተፈጥሮ ላይ የሚደረገዉ ብዝበዛም እፀዋት እንዲደርቁ፤ ብሎም ዘራቸዉ እንዲጠፋ፤ እንስሳትም በተመሳሳይ መልኩ ለእልቂት እንዲዳረጉ በማስገደዱ፤ ርሃብና ድህነት የሰዉ ልጅን ህይወት ተጎዳኝተዉ መኖር ከጀመሩ ዘመናት ተቆጥረዋል።

https://p.dw.com/p/E0mR
...............እንዴት ይጠበቅ
...............እንዴት ይጠበቅምስል dpa

በየአቅጣጫዉ ብዝሃ ህይወትን ስለመንከባከብና ስለመጠበቅ ይነገራል፤ በያዝነዉ ዓመት ደግሞ ለየት ባለ መልኩ በሚመስል አካሄድም በተለያዩ ጊዜያት ትላልቅ ጉባኤዎች መካሄድ ይዘዋል። ብዝሃ ህይወትን የመጠበቁ ነገር ታዲያ በተለይ በድሃ አገራት የሚገኘዉን ማህበሰብ ህይወት በማይጎዳ መልኩ እየተደረገ ነዉ ወይ?