1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቬስተርቨለ የሊቀመንበርነት ሥልጣን መልቀቅ

ሰኞ፣ መጋቢት 26 2003

በቅርቡ በሁለት ፌደራል ክፍላተ- ሀገር በተካሄዱ፣ ም/ቤታዊ ምርጫዎች ከባድ ሽንፈት ያጋጠመው የነጻ ዴሞክራቱ ፓርቲ (FDP) ፣ በሊቀመንበሩ በውጭ ጉዳይ

https://p.dw.com/p/RFIp
ምስል dapd

ሚንስትሩ  ጊዶ ቬስተርቨለ ላይ ግፊት በማጠናከሩ ፤ ቬስተርቨለ ፣ በትናንቱ ዕለት የፓርቲውን ሊቀመንበርነት ሥልጣን ከግንቦት አንስቶ መልቀቃቸውን ከማስታወቃቸውም ፤  የምክትል መራኄ-መንግሥትነቱን ሥልጣንም እንደሚተውና በውጭ ጉዳይ ሚንስትርነት ሥልጣናቸው ብቻ እንደሚቆዩ  ገልጸዋል። ፓርቲው ዛሬ አዲስ ሊቀመንበር ሳይመርጥ አይቀርም ተብሎ ይጠበቅ ነበረና፤ በዚህ ጉዳይ ላይ የተከታተለውን ፤ የበርሊኑን ዘጋቢአችንን ይልማ ኃይለ-ሚካኤልን ጠይቄ ነበር----

ይልማ ኃ/ሚካኤል

ተክሌ የኋላ

ሒሩት መለሰ