1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የተመድ የናይሮቢዉን ጥቃት በጥብቅ አወገዘ

እሑድ፣ መስከረም 12 2006

የተመድ የፀጥታዉ ጥበቃ ምክር ቤት በኬንያ ናይሮቢ፤ ገበያ ማዕከል የተከሰተዉን ደም አፋሳሽ ጥቃት በጥብቅ አወገዘ። አሸባሪነት የዓለማቀፍን ሰላምና ጸጥታ የሚያደፈርስ ግዙፍ ጠንቅ ነዉ ሲል፤ በኒዮርክ የሚገኘዉ የተመድ ጽ/ቤት አስታዉቀዋል።

https://p.dw.com/p/19m2h
A police officer holds a gun to provide cover for customers running out as a shooting took place at Westgate shopping mall in Nairobi September 21, 2013. Kenyan soldiers joined an operation to flush out gunmen who killed at least 15 people in a shopping centre in the capital of Nairobi on Saturday, a Reuters witness said. REUTERS/Noor Khamis (KENYA - Tags: CIVIL UNREST CRIME LAW TPX IMAGES OF THE DAY)
ምስል Reuters

በናይሮቢ «ዌስት ጌት» በተባለ የገበያ ማዕከል በደረሰዉ አስከፊ ጥቃት እስካሁን 59 ሰዎች መገደላቸዉን እና ወደ 200 ሰዎች መቁሰላቸዉን የሀገሪቱ መንግስት አስታዉቋል። ከሟቾቹ መካከል የዉጭ አገር ዜጎች ይገኙበታል። የኬንያ ፖሊስ እንዳስታወቀዉ ትናንት ቅዳሜ 18 ጨንበል ያጠለቁ ታጣቂዎች፤ ዊስት ጌት በተሰኘዉ፤ የገበያ ማዕከል ሰርጎ በመግባት የተኩስ ሩምታ ከፍተዋል። የእጅ ቦንብ አፈንድተዉ ከባድ ጥቃት አድርሰዋል። በመገበያያ ማዕከሉ አጋቾች ቦታውን በመቆጣጠር፤ ከፖሊስ ጋር ከበድ ያለ የመሳሪያ ልውወጥ ማድረጋቸውን እና ዛሬ እሁድ በተደጋጋሚ የማሳሪያ ድምጽ መስማታቸውን በቦታው የሚገኙ የአይን እማኞች ተናግረዋል፡፡ ከሟቾች መካከል የፕሪዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ እህት ልጅ እና እጮኛዉ፤ ሳይኖሩበት እንዳልቀረም ተገልጾአል።
የኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬኒያታ ጥቃቱን አስመልክቶ ባሰሙት ንግግር ሁሉም አጋቾች የትም ቢገቡ ተይዘው ቅጣትን እንደሚቀበሉ ቃል ገብተዋል፡፡ በዚህ ጥቃትም ኡሁሩ ኬንያታ፤
«በዚህ ጥቃት የቤተሰብ አባላትን ላጡ ወገኖች ሃዘኔን እገልጻለሁ። ምን አይነት የሃዘን ስሜት ዉስጥ እንዳሉ መገመት አይሳነኝም፤ ምክንያቱም እኔም በዚህ ጥቃት በጣም ቅርብ ዘመዶቼን አጥቻለሁ» ፖሊስ ምን ያል አጋቾች በህንጻው ውስጥ እንዳሉ መረጃው ባይኖረውም ፤ የኬንያ የሀገር አስተዳደር ሚኒስቴር ጆሴፍ ኦሌ ሊንኩ ከ10 እስከ 15 የሚሆኑ ታጣቂዎች ታጋቾችን ይዘዉ በገበያ ማዕከሉ ህንጻ ዉስጥ ተደብቅዉ ሳይኖሩ እንደማይቀር ገልጸዋል። በኬንያ የሀገር አስተዳደር ሚኒስትር ጆሴፍ ኦሌ ሊንኩ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ
« ስለ ዝርዝር ጉዳዮ አሁን ምንም መናገር አንሻም፤ ነገር ግን የኬንያ የፀጥታ ጥበቃ አባላት ሁኔታዉን ሙሉ በሙሉ ቁጥጥር ስር ማድረጋቸዉን መግለፅ እወዳለሁ። አሁን ሁላችሁንም ማመስገን እፈልጋለሁ። በቀጣይ ስለሚፈጠረዉ ክስተት ምናልባትም በአንድ ሰዓት ግዜ ዉስጥ እናሳዉቃችኋለን። አሁን እባካችሁ በቀጣይ መሰራት ያለበት ጉዳይ ተግባራዊ እንድናደርግ ልቀቁን» ብሪታንያ እስካሁን በናይሮኒዉ ጥቃት በጥቂቱ ሶስት ዜጎችዋ እንደተገደሉባት የብሪታንያ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታዉቋል።
በሶማልያ የሚንቀሳቀሰዉና ከአልቃይዳ ጋር ግንኙነት እንዳለዉ የሚነገርለት የደፈጣ ተዋጊ ቡድን አልሸባብ ለጥቃቱ ኃላፊነቱን እንደሚወስድ አሳውቋል፡፡
በሌላ በኩል እስካሁን የገበያ ማዕከልን ከአጋቾች ለማስለቀቅ በሚደረግ ጥረት ላይ እስራኤላዉያን አማካሪዎች የኬንያን ወታደራዊ ሃይሎችን በስልታዊ አሰራር ምክርን በመስጠት ላይ መሆናቸዉን የእስራኤል መንግስት ገልጾአል። 59 ሰዎች የተገደሉበት የናይሮቢዉ ዌስት ጌት የገበያ ማዕከል በከፊል የእስራኤላዉያን እንደሆነ ተመልክቶአል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በኬንያ ድህረ ፕሬዚደንታው ምርጫ፤ በተከሰተው ግጭት በስብዕና ላይ ወንጀል ፈፅመዋል በሚል ክስ፤ ደን ኻግ በሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት የጦር ወንጀለኞች መርማሪ ፍርድ ቤት የቀረቡት፤ የኬንያ ምክትል ፕሬዚደንት የዊልያም ሩቶ ጠበቆች፤ በኬንያ የተከሰተዉን ጥቃትን ለመከታተል ሩቶ ወደ ሀገራቸዉ መመለስ እንዲችሉና የፍርድ ሂደቱ ለሌላ ግዜ ቀነቀጠሮ እንዲሰጠዉ መጠየቃቸዉ ታዉቋል።

Police take cover outside Westgate shopping centre where gunmen went on a shooting spree in Nairobi September 21, 2013. The gunmen stormed the shopping mall in Nairobi on Saturday killing at least 15 people in what Kenya's government said might be a terrorist attack, and sending scores fleeing into shops, a cinema and onto the streets in search of safety. Sporadic gun shots could be heard hours after the assault started as soldiers surrounded the mall and police combed the building, hunting down the attackers shop by shop. Some local television stations reported hostages had been taken, but there was no official confirmation. REUTERS/Goran Tomasevic (KENYA - Tags: CIVIL UNREST TPX IMAGES OF THE DAY)
ምስል Reuters
Armed police search through Westgate shopping centre for gunmen in Nairobi, September 21, 2013. Gunmen stormed the shopping mall in the Kenyan capital on Saturday killing at least 15 people, according to the Kenyan Red Cross, and sending scores fleeing into shops, a cinema and onto the streets seeking safety. REUTERS/Goran Tomasevic (KENYA - Tags: CIVIL UNREST CRIME LAW TPX IMAGES OF THE DAY)
ምስል Reuters

አዜብ ታደሰ

ልደት አበበ