የተ.መ.ድ ጉባኤና የባራክ ኦባማ ንግግር
ረቡዕ፣ መስከረም 16 2005ማስታወቂያ
ኒውዮርክ ውስጥ በመካሄድ ላይ ባለው 67 ተኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጉባኤ የመንግሥታት መሪዎች ዛሬም ንግግር ማድረጋቸውን ቀጥለዋል ። ትንንት በድርጅቱ አመታዊ ጉባኤ መክፈቻ ስነ ስርዓት ላይ ንግግር ካደረጉት መሪዎች አንዱ የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝዳንት ባራካ ኦባማ ናቸው ። ኦባማ ለጉባኤው ባሰሙት ንግግር በተለይ ኢራን የኒዩክልየር ጦር መሣሪያ ባለቤት እንዳትሆን አስፈላጊውን ሁሉ እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል ። ሙስሊሞችን ባስቆጣው ፊልም ምክንያት በሙስሊም አገራት በሚገኙ የአሜሪካ ኤምባሲዎች ላይ የተሰነዘሩትን ጥቃቶችና የተከተሉትን አመፆችም በዲሞክራሲ ላይ ያነጣጠሩ በማለትም አውግዘዋል ። ዝርዝሩን የዋሽንግተ ዲሲው ዘጋቢኢችን አበበ ፈለቀ ልኮልናል ።
አበበ ፈለቀ
ሂሩት መለሰ
ሸዋዮ ለገሰ