1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የተመ የጠቅላላ ጉባዔ ሊቀመንበር በአፍሪቃ ኅብረት 

ዓርብ፣ መጋቢት 22 2009

ትናንት አዲስ አበባ የሚገኘዉ የአፍሪቃ ኅብረት ዋና ፅሕፈት ቤት የጎበኙት የተመ የጠቅላላ ጉባዔ የዓመቱ ሊቀመንበር ፒተር ቶምሰን፤ ከኅብረቱ መሪዎች ጋር መወያየታቸዉ ተገለጸ። ቶምሰን 0 በመቶዉ የሚሆኑት ያላደጉ ሃገራት የሚገኙት አፍሪቃ ዉስጥ

https://p.dw.com/p/2aTIO
Afrikanische Union Gebäude Außenansicht Äthiopien Addis Ababa
ምስል Imago

Ber. A.A (Zusammenarbeit zwischen UN und AU_Peter Thomson besuch) - MP3-Stereo


ትናንት አዲስ አበባ የሚገኘዉ የአፍሪቃ ኅብረት ዋና ፅሕፈት ቤት የጎበኙት የተመ የጠቅላላ ጉባዔ የዓመቱ ሊቀመንበር ፒተር ቶምሰን፤ ከኅብረቱ መሪዎች ጋር መወያየታቸዉ ተገለጸ። ከመላዉ ዓለም 70 በመቶዉ የሚሆኑት ያላደጉ ሃገራት የሚገኙት አፍሪቃ ዉስጥ መሆኑን ያመለከቱት ቶምሰን፤ በአብዛኞቹ ሃገራት ዘላቂ ሰላምን እና ፀጥታን ለማስበር ከፍተኛ ትግል እያደረጉ መሆኑን አፅንኦት ሰጥተዋል። ከዚህም ሌላ በአፍሪቃ ቀንድ ስለተከሰተዉ ረሃብ በተለይም ደግሞ በደቡብ ሱዳን ስላለዉ ወቅታዉ ሁኔታ ከአፍሪቃ ኅብረት ባለስልጣናት ጋር ተወያይተዋል።   


ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ


አዜብ ታደሰ
ሸዋዬ ለገሰ