1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የተረሱ የአፍሪቃ ስደተኞች

ሰኞ፣ የካቲት 20 2009

የተመ የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን እንደሚለው አፍሪቃ ውስጥ 16ሚሊዮን ስደተኞች በተለያዩ መጠለያዎች ውስጥ ይገኛሉ። ከነዚህም ጎስቃላ ህይወት የሚገፉት ጥቂት የሚባሉ አይደሉም ።  ታንዛንያ በሚገኝ መጠለያ የተጠጉ የብሩንዲ ስደተኞች የዚህ አንድ ምሳሌ ናቸው ።

https://p.dw.com/p/2YJVa
Tansania - Flüchtlinge aus Burundi
ምስል DW/K. Tiassou

Tansania Flüchtlinge - MP3-Stereo

ካሪን ለቤተሰቦችዋ ምሳ እየሰራች ነው ።ሁሌም እንደምታደርገው የበቆሎ ገንፎ እና ጥቂት አተር እያዘጋጀች ነው ። በየቀኑ ማለት ይችላል ፣ ይህን ነው የምንበላው ይላል ባለቤትዋ ማይክል
«ያለን አተር እና የበቆሎ ገንፎ ብቻ ነው ። ከ5 ቀናት በኋላ ያልቃል ። አዲሱ ራሽን እስከ ሚሰጠን ድረስ 4 ቀናት ይቀራሉ ። ምግብ እስኪገኝ ድረስ ከልጆቻችን ጋር እንጠብቃለን ፤ ምንም ማድረግ አንችልም ። »
ማይክል ታንዛንያ የገባው የ32 ዓመቷን ባለቤቱን፣ አራት ልጆቹን እና የባለቤቱን አያት ይዞ ነው ። በብሩንዲው ፕሬዝዳንት ፕየር ንኩሩንዚዛ ላይ ተሞክሮ ከከሸፈው መፈንቅለ መንግሥት በኋላ ግንቦት 2015 ነበር ታንዛንያ የመጣው። ያኔ በአስር ሺህዎች የሚቆጠሩ የብሩንዲ ዜጎች  ሸሽተዋል ። የተመ የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን ባልደረባ አማህ አስያማ ብዙዎቹ የወጡት አስቸጋሪ ሁኔታዎችን አልፈው መሆኑን ያስታውሳሉ ። 
« ከዚህ በጀልባ ሦስት ሰዓት ካጉንካ የሚባል አንድ ሐይቅ ዳር የሚገኝ መንደር ውስጥ ያለ ስፍራ ቁጥራቸው 60 ሺህ የሚደርስ ስደተኞች ይገኙ ነበር ። ምን ነገር አልነበራቸውም ። የአካባቢው ነዋሪዎች  ምንም ባይኖራቸውም ፤በአካባቢው ኮሌራ እስከገባበት ጊዜ ድረስ እነርሱን አስጠጉዋቸው ነበር »
ከመካከላቸው በትኩሳት እና የሰውነታቸው ውሐ በመቀነሱ በጣም የታመሙት ናያሩጊሲ ተወስደው ነበር ። በአንድ ጉዞ በአንድ አሮጌ የጀርመን ጦር መርከብ 300 ሰው እየተጫነ ሁሉንም ለማጓጓዝ ሁለት ሳምንታት ወስዷል ። « ስደተኞቹን ከካኩንጋ ማውጣትን ጨምሮ ግባችን በየትኛውን መንገድ ህይወት ማትረፍ ነበር ።ይህ ተሳክቶልናል ። ሆኖም በመጠለያ ብዙ ችግሮች አሉ ።
የማይክል ቤተሰብ የተመድ በሰጣቸው አንዲት አነስተኛ ድንኳን ውስጥ ነው የሚኖረው ። ድንኳኑ አገልግሎት እነርሱን ካስጠለለ ሁለት ዓመት ይጠጋል ። በዚህ ጊዜ ዝናብና ፀሐይ የተፈራረቀበት ይኽው ድንኳን አሁን ይዞታው ጥሩ አይደለም  ። 
«ድንኳኑ ከላይ ቀዳዳ አለው። ውሐ ይገባበታል ። ሰባት ሆነን ነው ድንኳኑ ውስጥ የምኖረው አጠገቡ ደግሞ ብዙ ሰዎች በጋራ የሚጠቀሙባቸው መፀዳጃ ቤቶች አሉ። የተሠሩት ለብዙ ሰዎች ታስበው አልነበረም እና እጅግ ቆሻሻ ናቸው ንፅህናቸው አይጠበቅም ። ። »
ድንኳኖቹ ተጠጋግተው ነው የተተከሉት ። ንያሩጉሱ እና በታንዛንያ ምዕራባዊ ድንበር ላይ የሚገኙት ሁለት ሌሎች የስደተኞች መጠለያዎች በስደተኞች ተጨናንቀዋል ። በአሁኑ ጊዜ በነዚህ መጠለያዎች  ከ200 ሺህ በላይ የብሩንዲ ስደተኞች ይገኛሉ ። በየቀኑ ከ300 የሚበልጡ አዳዲስ ስደተኞች ይገባሉ ።ሌላ አራተኛ ካምፕ ለመሥራት ጥያቄ ቀርቧል ። ገና ፈቃድ አልተገኘም ። የ UNHCR ዋ አማህ አሲያማ እንደሚሉት ጎስቋላዎቹን ድንኳኖች በሌላ መተካት፣ ምግብ ማብሰያ መብራት እና አዳዲስ የውሐ ማጠራቀሚያ ያስፈልጋል ።በቂ ሆስፒታሎችም ሆነ መድሐኒቶች የሉም ። UNHCR ባለፈው ዓመት በብሩንዲው ቀውስ ለተሰደዱት መርጃ የሚውል የ180 ሺህ ዶላር እርዳታ ጠይቆ ነበር ። የተገኘው ግን ከተጠየቀው ግማሽ ያህሉ ብቻ ነው ።
«ዓለም ዓቀፉ ማህበረሰብ በቂ ገንዘብ አልለገሰም ማለት አልችልም ። ምክንያቱም በዓለማችን ብዙ ሰብዓዊ ቀውሶች እንዳሉ  እናውቃለን ። በሚያሳዝን ሁኑታ እኛ ጋ ያለው የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ እንደሌሎቹ ትኩረት አላገኘም ። በዚህ ምክንያት እዚህ በጣም በጣም አስቸጋሪ ነበር ።»
ይሁን እና ቤተሰቦቹን በሙሉ ብሩንዲ  ላጣው ለስደተኛ ፍራንክ ግን ከመሞት የማይሻል ነገር የለም 
«እውነት ነው እዚህ የድህነት ህይወት ነው ያለው። ሆኖም ከመሞት የተጎሳቀለ ህይወት ይሻላል ። የወላጆቼ እና የወንድም እህቶቼ ደም የፈሰሰበት ቡሩንዲ ተመልሼ መሄድ አልችልም ሌላ ቦታ ብሞት ይሻለኛል ። »

Tansania - Flüchtlinge aus Burundi
ምስል DW/K. Tiassou
Ruanda Kagunga Flüchtlinge
ምስል DW/Prosper Kwigize

ሊንዳ ሽታውደ/ ኂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሠ