1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የተራዘመዉ የፓሪሱ የአየር ንብረት ተመልካች ጉባዔ

ዓርብ፣ ታኅሣሥ 1 2008

አዲስ ረቂቅ ይዞ ዛሬ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቅ የነበረዉ የፓሪሱ የተመድ የአየር ንብረት ለዉጥ ተመልካች ጉባዔ መስማምያ ነጥብ ላይ ባለመደረሱ ለአንድ ቀን መገፋቱ ተነገረ።

https://p.dw.com/p/1HM5C
paris klima ban COP21 le bourget UN
ምስል picture-alliance/AP Photo

10 ቀኑን የያዘዉ ይህ ጉባዔ ሚኒስትሮች በመካከላቸዉ ያለዉን ጥልቅ የሃሳብ ልዩነት ለመፍታት ለሊቱን ሙሉ ቢደራደሩም ነጥብ ላይ ባለመድረሳቸዉ ነዉ ልዩነታቸዉን ለማጥበብ የመጠናቀቅያዉን ቀን ለነገ ቅዳሜ እንዳዛወሩት የተመለከተዉ። ይህን ጉባዔ የሚመሩት የፈረንሳዩ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሎውሮ ፋቢዩስ ዉይይቱ ከተጠበቅነዉ በላይ አንድ አዲስ የመግባብያ ረቂቅ ነጥብ ላይ እንደሚደርስና በቀና መንገድ እየተከናወነ መሆኑን በሙሉ ልብ ተናግረዋል። 195 የዓለም አገራት የሚሳተፉበት የፓሪሱ ጉባዔ የከባቢ አየር ሙቀትን 2,0 ዲግሪ ሴልሽየስ በታች ለመቀነስና ዓለም ላይ ሊከተል የሚቸለዉን አደጋ በመከላከል መፍትሄ ላይ ለመድረስ ነዉ።

ይልማ ኃይለሚካኤል

አዜብ ታደሰ

ሂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ