1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የተቀበሩ ፈንጅዎች የሚጠረጉበትና መሬቱ ለልማት የሚዘጋጅበት ርምጃ

ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 14 1997

በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል ለሁለት ዓመታት የተካሄደው የድንበሩ ጦርነት ያንኑ የድንበር አካባቢ በፈንጅ ወጥመድ በክሎታል።

https://p.dw.com/p/E0f8

ይኸው ፈንጅ-ወጥመድ እስካሁን በአካባቢው ሕዝብ ላይ ከባድ የአካል ጉዳትና የሞት አደጋ ሲያስከትል ነው የቆየው። ሆኖም አሁን በመካሄድ ላይ የሚገኘው የፈንጅ ማምከኛውና መጥረጊያው ሥራ ለሕዝቡ አካላዊ ደኅንነት ብቻ ሳይሆን፣ ለግብርናው፣ ለኤኮኖሚያዊው ልማት ጭምር መድኅን የሚሆንበን ተሥፋ ነው የፈነጠቀው። ይህንኑ በአትኩሮት የተመለከተው ወኪላችን ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር የዚሁኑ የፈንጅ ማምከን ሥራ ኃላፊዎች አነጋግሮ ከመቐለ ያስተላለፈልን ዘገባ የዛሬውን መርሐግብር ይሸፍናል። ይህንኑ ዘገባ እነሆ ከዚህ ቀጥሎ አዳምጡት፥