1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የተቃውሞ ሰልፍ

ረቡዕ፣ መስከረም 25 2009

በቅርቡ ኢትዮጵያን ይጎበኛሉ ተብለው የሚጠበቁት የጀርመን መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል ፣መንግሥት የሰብዓዊ መብት ረገጣን እንዲያቆም ተጽእኖ እንዲያደርጉ አሳስበዋል ።

https://p.dw.com/p/2QuhW
Deutschland Demonstration in Berlin gegen Verletzungen der Menschenrechte in Äthiopien
ምስል DW/Y. H. M. Korri

ጀርመን በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ግፊት እንድታደርግ ተጠየቀች ። በቢሾፍቱ የደረሰውን ሞት በመቃወም ዛሬ የጀርመን ርዕሰ ከተማ በርሊን ሰልፍ የወጡ ኢትዮጵያውያን እና ጀርመናውያን የመብት ተሟጋቾች በቅርቡ ኢትዮጵያን ይጎበኛሉ ተብለው የሚጠበቁት የጀርመን መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል ፣መንግሥት የሰብዓዊ መብት ረገጣን እንዲያቆም ጫና እንዲያደርጉ አሳስበዋል ። አንዳንድ የሰልፉ እንድምተኞች ደግሞ የሜርክል የኢትዮጵያ ጉብኝት ጊዜውን የጠበቀ ስላይደለ ባይሄዱ ይመረጣል ብለዋል ። የሰልፉን ሂደት የተከታተለው የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ኃይለ ሚካኤል ዝርዝር ዘገባ አዘግጅቷል .

ይልማ ኃይለ ሚካኤል

ኂሩት መለሰ

አዜብ ታደሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ