1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የተቋረጠው የደቡብ ሱዳን የሰላም ንግግር

ዓርብ፣ ነሐሴ 2 2006

በዚህ ሳምንት ሰኞ አዲስ አበባ ውስጥ የተጀመረው የሰላም ንግግር የተቋረጠው ተቃዋሚው SPLM A አንዳንድ ተወካዮች በንግግሩ ላይ መሳተፋቸውን በመቃወሙ መሆኑን የድርድሩ ተካፋይ የሆኑት የሴቶች ተወካይ ለዶቼቬለ ተናግረዋል ።

https://p.dw.com/p/1CrbT
Südsudan Friedensverhandlung in Addis Abeba Dr Dhieu Mathok
ምስል DW/G.Tedla

የደቡብ ሱዳን ተፋላሚ ኃይሎች ከዚህ ቀደም የተቋረጠውን የሰላም ንግግር በዚህ ሳምንት ሰኞ እንደገና ቢቀጥሉም በተከታታይ ቀናት ንግግሩን አላካሄዱም ። ከዚህ ቀደም የተስማሙባቸውን የተኩስ አቁም ውሎችም አሁንም እንደተጣሱ ነው ። በዚህ ሳምንት ሰኞ አዲስ አበባ ውስጥ የተጀመረው የሰላም ንግግር የተቋረጠው ተቃዋሚው SPLM A አንዳንድ ተወካዮች በንግግሩ ላይ መሳተፋቸውን በመቃወሙ መሆኑን የድርድሩ ተካፋይ የሆኑት የሴቶች ተወካይ ለዶቼቬለ ተናግረዋል ። ሁለቱ ወገኖች ንግግሩን እንዲቀጥሉ አደራዳሪው የምሥራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግሥታት ባለሥልጣን ኢጋድ እየጣረ ነው ።ኢጋድ በተለይ SPLM A በአስቸኳይ ወደ ድርድሩ እንዲመለስ አስጠንቅቋል ። የአዲስ አበባው ወኪላችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ዝርዝር ዘገባ አለው ።

ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ

ኂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ