1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰላም ተልዕኮ

ዓርብ፣ ግንቦት 21 2001

ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰላም ማስከበር ተልዕኮዎች በጣት የሚቆጠሩት ብቻ ናቸው የተሳኩ ሊባሉ የሚችሉት ። ሉድገር ሻዶምስኪ እንደዘገበው ከፍተኛ ገንዘብ ከሚፈስባቸው ከነዚህ ተልዕኮዎች አብዛኛዎቹ በውጤት አልባነት ይተቻሉ ።

https://p.dw.com/p/I0F4
ምስል picture-alliance/ dpa

በአሁኑ ጊዜ ቁጥራቸው 113,000 የሚደርስ ወታደሮች ፖሊሶች ሲቪል ሰራተኞችና አማካሪዎች በአራት ክፍለ ዓለማት ውስጥ በሚገኙ አስራ ስድስት የተባበሩት መንግስታት የሰላም መስከበር ተልዕኮች ውስጥ እያገለገሉ ነው ። ይህ አሀዝ እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር ከ1999 ኙ ጋር ሲነፃፀር ከሰባት ዕጥፍ በላይ አድጓል ። የመንግስታቱ ድርጅት እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር ከሀምሌ 2007 እስከ ሰኔ 2008 የሰላም ተልዕኮው ዓመታዊ ወጪ ሰባት ቢሊዮን ዶላር ሲሆን ይህም ከአጠቃላዩ የዓለም ወታደራዊ ወጪ ነጥብ አምስት(.5) በመቶ ነው ። ይህ ሁሉ ገንዘብ ከሚፈስበት የሰላም ተልዕኮ አብዛኛው በውጤት አልባነት ይተቻል ።

ሂሩት መለሰ

ተክሌ የኋላ