1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአቶ ግርማ ሰይፉ መጽሐፍ ምረቃ በቶሮንቶ

ማክሰኞ፣ መስከረም 23 2010

የቀድሞው የአንድነት ለዴሞክራሲ እና ለፍትህ ፓርቲ የምክር ቤት አባል አቶ ግርማ ሰይፉ በቅርቡ ለንባብ ያበቁት «የተከበሩት» መጽሐፍ የሚያተኩረው በምክር ቤት ቆይታቸው ስለነበራቸው ተሞክሮ እና በዚያን ጊዜ ስለታዘቧቸው ጉዳዮች እንደሆነ ለዶቼቬለ ተናግረዋል። በተጨማሪም ፓርላማ ወክለው የገቡለት ፓርቲ ክፍፍል ጉዳይንም እንደሚዳስስ ገልጸዋል።

https://p.dw.com/p/2l9g7
Buchstart von Girma Seifu
ምስል DW/A. Negash

የአቶ ግርማ መጸሐፍ ምረቃ

የቀድሞ የኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል አቶ ግርማ ሰይፉ በቅርቡ ያሳተሙትን መጽሐፍ በሰሜን አሜሪካ ከተሞች እያስመረቁ ነው። አቶ ግርማ ሰሞኑን ቶሮንቶ ካናዳ በተካሄደው የምረቃ ስነ ስርዓት ላይ ከዶቼቬለ ጋር ቃለ ምልልስ አድርገው ነበር። «የተከበሩት» የተሰኘው መጽሃፋቸው በምክር ቤት ተሞክሮአቸው እና ትዝብታቸው እንዲሁም ወክለው ፓርላማ የገቡለት የአንድነት ለዴሞክራሲ እና ለፍትህ ፓርቲ ክፍፍል ላይ እንደሚያተኩር ተናግረዋል። አቶ ግርማ ሰይፉ ከ2003 እስከ 2007 ዓም በኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ብቸኛው ተቃዋሚ የምክር ቤት አባል ነበሩ። አክመል ነጋሽ ከቶሮንቶ ዝርዝሩን ልኮልናል።

አክመል ነጋሽ 
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ