1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የተገን ጠያቂዎች ቁጥር መጨመር

ሐሙስ፣ መጋቢት 20 2004

ባለፈው ዓመት በሰደተኞች ተጨናንቃ የከረመችው የኢጣልያዋ ደሴት ላምፔዱዛ አሁን መተንፈሻ ጊዜ አግኝታለች ። ደሴቲቱ አምና በተለይ ከአፍሪቃ በሚጎርፉ ስደተኞች ተጥለቅልቃ ነበር ። የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር በእንግሊዘኛው

https://p.dw.com/p/14Uwm
ምስል picture-alliance/dpa

ባለፈው ዓመት በሰደተኞች ተጨናንቃ የከረመችው የኢጣልያዋ ደሴት ላምፔዱዛ አሁን መተንፈሻ ጊዜ አግኝታለች ። ደሴቲቱ አምና በተለይ ከአፍሪቃ በሚጎርፉ ስደተኞች ተጥለቅልቃ ነበር ። የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር በእንግሊዘኛው ምህፃር UNHCR እንዳሰታወቀው በንፅፅር ሲታይ ኢጣልያና ማልታ እጎአ ከ 2010 ይልቅ በ 2011 እጅግ በዙ የተገን ጠያቂዎች ማመልከቻዎች ደርሰዋቸዋል ። ቱርክም እንደ ቀድሞው ከኢራቅ ብቻ ሳይሆን ከሶሪያ የመጡ ስደተኞቸንም ጭምር ስታስተናግድ ከርማለች ።

Tunesien Libyen Grenze Afrikanische Flüchtlinge
ምስል DW

የዶቼቬለዋ ሞኒካ ግሪብለር በ 2011 በዓለም ዙሪያ የጥገኝነት ማመልከቻዎችን ሁኔታ ቃኝታለች እጎአ በ 2011 በኢንዱስትሪ በበለፀጉት ሃገራት 441,300 የጥገኝነት ማመልከቻዎች ቀርበዋል ። ይህም ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር በ20 በመቶ ገደማ ከፍ ያለ ነው ፤ በአውሮፓ በሰሜን አሜሪካ በፓስፊክ ና በሰሜን ምሥራቅ እስያ በሚገኙ 44 ሃገራት የስደተኞችን ሁኔታ በተመለከተው የUNHCR ባቀረበው ዘገባ መሠረት ።

Karl Kopp Europareferent PRO ASYL
ካርል ኮፕምስል Pro Asyl

አሃዛዊ መረጃዎቹ የአረቡ ዓለም ህዝባዊ አመፅ ፣ የሶሪያው ብጥብጥ እንዲሁም የአፍሪቃ ደም አፋሳሽ የሥልጣን ትግል ነፀብራቅ ናቸው እንደ ግሪብለር ። የተገን ጠያቂዎች ቁጥር መጨመርም 2011 ለብዙዎች እጅግ አሰቸጋሪ ዓመት እንደነበረ አመልክች መሁኑን የ UNHCR ኮሚሽነር አንቶንዮ ጉተሬስ አሰታውቀዋል ። Pro Asyl በተባለው ለተገን ጠያቂዎች መበት ተቆርቋሪው ድርጅት የአውሮፓ ጉዳዮች ተከታታይ ካርል ኮፕም ዓመቱ በዓይነቱ የተለየ እንደነበረ ነው የሚናገሩት ።
« የሰደተኞቹ ቁጥር ሳይሆን ሁኔታው በጣም ተባብሷል ። 2011 በአውሮፓ የሰደተኞች መርህ ታሪክ የተባባሱ ሁኔታዎች የታዩበት ዓመት ነበር ። ክ2 ሺህ በላይ የሚሆኑ ከሊቢያና ከቱኒዝያ ወደ ኢጣልያ ያቀኑ ሰዎች በጉዞ ላይ ህይወታቸውን አጥተዋል ። »


አምና በተለይ ከከኮት ዲቯርና ከሊቢያ እንዲሁም ከሶሪያ ተሰደው ጥገኝነት የሚጠይቁ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ አድጓል ። እነዚህ ሃገራት በሙሉ ደም አፋሳሽ ግጭቶች የደረሱባቸው ናቸው ። በአፍጋኒስታን በቻያና እና በኢራቅም ሁኔታዎች አመቺ ባለመሆናቸው ባለፈው ዓመት ብዙዎች ሃገራቸውን ጥለው ተሰደዋል ። ከጥገኝነት ጠያቂዎች አብዛኛዎቹ ከነዚህ ሃገራት ነው የመጡት ።
የሃገራቸው ግጭት ሸሽተው ወደ ሶሪያ የተሰደዱ በርካታ ኢራቃውያን የሶሪያው የርስ በርስ ጦርነት ሰለባ ሆነዋል ። አፍጋናውያን ሰደተኞች ደግሞ ከገቡባቸው ከኢራንና ከፓኪስታን እንዲወጡ ግፊት እየተደረገባቸው ነው እንደ ኮፕ ።
«ፓኪስታንና ከኢራንን ከመሳሰሉ ከተቀባይ ሃገራት በኩልም ስደተኞቹ ወደ መጡበት ወደ አፍጋኒስታን እንዲመለሱ ጠንካራ ግፊት አለ ። የደህንነት ዋስትና መታጣቱም ሰደተኞች ቀሰ በቀስ በሌሎች ሃገራት ጥገኝነት መጠየቅ እንዲሞክሩ ያደርጋል ። ብዙዎች በአውስትሬሊያና በአውሮፓ
ጥገኝነት ለማግኘት ይሞክራሉ ። »

Tunesien Libyen Grenze Afrikanische Flüchtlinge Flash-Galerie
ምስል DW


በ2011 የአውሮፓ ሃገራት 327,200 የጥግኝነት ማመልከቻውችን በመቀበል የመጀመሪያውን ደረጃ ይዘዋል ። ዩናይትድ ስቴትስ ደግሞ በ 99,400 ማመልከቻዎች ሁለተኛው ደረጃ ላይ ትገኛለች ። ጀርመን ደግሞ 45,741 ተገን ጠያቂዎች ማመልከቻዎች ደረርሰዋታል ። አብዛኛዎቹ ከአፍጋኒስታን ከኢራን ከሶሪያ እና ከፓኪስታን ናቸው ። በጃፓንና በደቡብ ኮሪያም አምና የተገን ጥያቄ ያቀረቡ ስደተኞች ቁጥር ለመጀመሪያ ጊዜ ከ 2010 በ 77 በመቶ ጨምሯል ። በተጨባጭ አሁን የተመዘገቡት ቁጥር ግን 2900 ብቻ ናቸው ። የዚህ ምክንያቱ ስደተኛው አማራጭ ፍለጋ ወደ ሌሎች ሃገራት መሻገሩ ነው ። « አውስትራሊያ አማራጭ አገር ናት ። አውስትራሊያ ግን ለምሳሌ በጅለባ በሚመጡ የአፍጋኒስታን ስደተኞች ላይ የምትከተለው መርህ ጠንከር ያለ ነው ። ይህ ምናልባትም ጠቋሚ እርምጃ ነወ ። በደቡብ አሜሪካም የተገን ጠያቂዎች ቁጥር እየጨመረ ነው ። ያም ማለት ጉዞው እየረዘመ ውድና አደገኛም እየሆነ በመሄድ ላይ ነው ። »
ዘንድሮም ብዙዎች አነዚህን አደገኛ ጉዞዎች ማደረጋቸው
እንደማይቀር ነው የሚገመተው ።

Illegale Immigranten provisorische Unterkunft Italien
ምስል picture-alliance/dpa

ሂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ