1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የተፈጥሮ ጥበቃ ግንዛቤ ከፍ ይበል

ማክሰኞ፣ መስከረም 19 2002

ለተፈጥሮ ቅጣት ዓለምን እየዳረገ የሚታየዉ ገደብ ያለፈዉ ብዝበዛና አግባብ ያልተከተለ አጠቃቀም እንደሆኑ ብዙዎች ይስማማሉ።

https://p.dw.com/p/Jto3
ይህንንም እኮ አረንጓዴ ማልበስ ይቻላል!ምስል dpa - Fotoreport

የዓለምን ሙቀት መጠን የጨመረዉ የአየር ጠባይ ለዉጥ በተለያዩ አካባቢዎች ልዩ ልዩ ችግሮችን ሲያስከትል እየታየ ነዉ። ተፈጥሮን በአግባቡ ካልያዝናት ከችግር ለመላቀቅና ድህነትን ለማስወገድ መንገዱ ይረዝማል የሚሉት የልማትና እድገት ባለሙያዎች ናቸዉ። እያንዳንዱ በየበኩሉ የሚሰራዉ ልማታዊ ተግባር ዉጤት እንዲኖረዉም ቅድሚያ የአካባቢ ተፈጥሮ ጥበቃ ግንዛቤዉን ማጎልበት ትርጉም ይኖረዋል።

ሸዋዬ ለገሠ/አርያም ተክሌ