1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቱርክና የሶርያ ፍጥጫና ግጭት

ሐሙስ፣ መስከረም 24 2005

ትናንት ከሶርያ ምድር በተወነጨፈ ሞርታር አምስት ዜጎቿ የተገደሉባት ቱርክ የአፀፋ ጥቃት ሰነዘረች። በሁለቱ ተጎራባች ሀገሮች መካከል የተካረረዉ ፍጥጫ እንዲረግብ የአዉሮጳ ኅብረት ሲያሳስብ፤ የሰሜን አትላንቲ የጦር ቃል ኪዳን ኔቶ በበኩሉ የሶርያን ርምጃ አዉግዟል።

https://p.dw.com/p/16JoL
ምስል Reuters

የጉዳዩን አሳሳቢነት በመግለፅም የተመድ የፀጥታዉ ምክር ቤትና ኔቶ አስቸኳይ ስብሰባ አካሂደዉ መግለጫ አዉጥተዋል። ቱርክ በኔቶ አባልነቷ የተባባሪ ሀገሮችን ድጋፍ ስትጠይቅ የሀገሪቱ መንግስትም እንዲሁ ሶርያ ላይ ወታደራዊ ርምጃ ለመዉሰድ በሚያስችለዉ ሁኔታ ላይ እየመከረ ነዉ።

ሸዋዬ ለገሰ

አርያም ተክሌ