1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ቱርክ ህዝበ ውሳኔ ውጤት

ሐሙስ፣ ሚያዝያ 12 2009

ዓለም አቀፍ ታዛቢዎች ህዝበ ውሳኔው ትክክለኛ እና ፍትሀዊ አልነበረም በማለት ዘገባዎች አውጥተዋል።የአውሮጳ ህብረትም የአንካራ መንግሥት ለህዝቡ ጥያቄ መልስ እንዲሰጥ ጥሪ አቅርቧል።

https://p.dw.com/p/2bctT
Türkei Proteste gegen Referendum in Istanbul
ምስል REUTERS/H. Aldemir

Beri. Brussels (Türkei Referendum-EU Rxn) - MP3-Stereo

ባለፈው እሁድ የተካሄደው የቱርክ ህዝበ ውሳኔ ውጤት ተቀባይነት የለውም ሲሉ የቱርክ መንግሥት ተቃዋሚዎች ያቀረቡትን አቤቱታ የቱርክ ምርጫ ቦርድ ውድቅ አድርጎታል።ተቃዋሚዎች የህዝበ ውሳኔው ሂደትም ሆነ ድምጽ አሰጣጡ ተጽእኖ የነበረበት፣ የተዛባ እና ትክክለኛ ያልሆኑ ካርዶች ጭምር ጥቅም ላይ የዋሉበት በመሆኑ ውጤቱን አንቀበልም ብለዋል።ዓለም አቀፍ ታዛቢዎች ህዝበ ውሳኔው ትክክለኛ እና ፍትሀዊ አልነበረም በማለት ዘገባዎች አውጥተዋል።የአውሮጳ ህብረትም የአንካራ መንግሥት ለህዝቡ ጥያቄ መልስ እንዲሰጥ ጥሪ አቅርቧል ። የብራሰልሱ ወኪላችን ገበያው ንጉሴ ዝርዝሩን ልኮልናል።  
ገበያው ንጉሴ 
ኂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ