1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቱርክ ፕሬዚዳንት የአፍሪቃ ጉብኝት

ዓርብ፣ ግንቦት 26 2008

የቱርኩ ፕሬዚዳንት ሬቼብ ጠይብ ኤርዶኻን የዚህ ሳምንት የኬንያ ዩጋንዳና ሶማልያ ጉብኝት ቱርክ ከሦስቱ ሃገራት ያላትን ግንኙነት የማጠናከር ጉልህ ሚና እንደሚኖረዉ ተገልፆአል። የአራት ቀን የአፍሪቃ ጉብኝታቸዉን ባለፈዉ ማክሰኞ ከዩጋንዳ የጀመሩት ኤርዶሃን ትናንት ኬንያን ዛሬ ደሞ ሶማልያን ጎብኝተዋል ።

https://p.dw.com/p/1J0GI
Afrka Uganda Erdogan
ምስል Getty Images/AFP/P. Busomoke

ኤርዶኻን ዛሬ በሶማልያ ጉብኝታቸዉ መዲና መቃዲሾ ላይ አዲስ የቱርክ ኤምባሲን መርቀዉ ከፍተዋል። ኤርዶዋን ሶማልያን ሲጎበኙ የዛሬዉ ለሦስተኛ ጊዜ መሆኑን አሶሽየትድ ፕሬስ ዘግቧል። የፕሬዚዳንት ኤርዶኻን የአፍሪቃ ጉብኝት ለቱርክ ምን ትርጉም ይኖረዉ ይሆን?

የቱርክ ፕሬዚዳንት በአሁኑ የአፍሪቃ ጉብኝታቸዉ በርካታ ልዑካንን አስከትለዉ ነዉ የተጓዙት። ኤርዶኻን በመቶዎች የሚቆጠሩ የምጣኔ ኃብት ባለሞያዎችን ይዘው በዩጋንዳና በኬንያ ያደረጉት ጉብኝት በአፍሪቃ የሚያገኙትን የኤኮኖሚ አድማሶች ሁሉ በማስፋት ከሃገራቱ ጋር ያላቸዉን ግንኙነት ለመገንባት ያለመ መሆኑ ነዉ የተገለፀዉ። አንድ የቱርክ ፕሬዚዳንት ዩጋንዳን ሲጎበኝ ኤርዶዋን የመጀመርያዉ በመሆናቸዉ ታሪካዊ ተብሎአል። የቱርክ ፕሬዚዳንት ቢሮ ባወጣዉ የጽሑፍ መግለጫ «ኤርዶኻን በአፍሪቃ የጀመሩት ፖለቲካዊ ጉብኝት ስኬታማ ነዉ» ሲል ነዉ ያስነበበዉ፤
በጀርመን ዚግን ከተማ የካቭካዝና ደቡባዊ አዉሮጳ ሃገራት ጥናት ተቋም ተጠሪ ክርስትያን ዮኃንስ ሃይንሪሽ እንደሚሉት የቱርክ አፍሪቃ ግንኙነት አዲስ አይደለም፤
« የቱርኩ ጠቅላይ ሚኒስትር ሜሱት ይልማዝ በነበሩበት ጊዜ ነዉ የቱርክ አፍሪቃ ግንኙነት በጎርጎረሳዉያኑ 1998 ዓ,ም የጀመረዉ። የዛን ጌዜ የጀመረዉ ይህ መርኃ ግብር ግን በቱርክ ዉስጣዊ ችግር ምክንያት ሙሉ በሙሉ ገቢራዊ መሆን አልቻለም ነበር። በዝያን ጊዜ ከሰሃራ በታች በሚገኙ አፍሪቃ ሃገራት 5% የኤኮኖሚ እድገት መታየቱ ፤ በተጨማሪም አፍሪቃ ከኤኮኖሚ አኳያ ጉልህ ሚና ያላት መሆኑም ታዉቆ ነበር። በቱርክ ይህ ኃሳብ በጎርጎረሳዉያኑ 2005 ዓ,ም ዳግም ተነስቶም ነበር። የአሁኑ የአፍሪቃ ግንኙነት መርኃ ግብር ከኤኮኖሚዉ ይልቅ በአፍሪቃ የሱኒ ሃይማኖትን በማኅበረሰቡ ለማስረፅ የታለመ ነዉ። በዩጋንዳና ኬንያ ደግሞ ከ 12 % በላይ የሚሆነዉ ማኅበረሰብ የሱኒ ሃይማኖት ተከታይ ነዉ»
እንደ ዮኃንስ ሃይንሪሽ በኬንያና ዩጋንዳ ፤ የሚኖረዉ የሱኒ ሃይማኖት ማኅበረሰብ ቁጥር እያደገ በመምጣቱ ቱርክ በተለይ ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር የማሰብዋ ምክንያት ከዚህ ጋር የተያያዘ ነዉ።
በኢስታንቡል የሃይንሪሽ ቦል ድርጅት ተጠሪ ክርስቲን ብራክል ኤርዶዋን አፍሪቃን የሚከተሉት ኃይማኖትን ተመርኩዘዉ ነዉ ብለዉ ያምናሉ። ለዚህም ሶማልያ ከቱርክ ጋር ያላትን ግንኙነት በምሳሌ እንደሚጠቅሱም ነዉ የገለፁት። ፕሬዚዳንት ኤርዶዋን በተደጋጋሚ እንደሚናገሩት «ስኬት አልባዉ ሃገር» ከሶማልያ ጋር ቱርክ የትብብር ሥራ በ«ሞዴልነት » የሚጠቀስ ይሉታል፤ ሲሉ ባርክል ተናግረዋል።
« ኤርዶኻን ሁሌ ከሚያሞካሽዋት ከሶማልያ ጋር ያለዉ ጉዳይ ሃይማኖትን በተመለከተ መሆኑ ግልፅ ነዉ። በመረሃ-ግብሩ ይዘት ግን ቱርክ ሌላ ፍላጎት እንዳላት ነዉ የሚያሳዩት። ኤርዶዋን እንደሚናገሩት ከምዕራባዉያን በበለጠ ሃገራቸዉ ከሶማልያ ጋር እንደምትሰራ ይናገራሉ። ለምሳሌ የልማት ትብብር ስራን በተመለከተ። ኤርዶኻን ለሶማልያን እንደተናገሩት፤ ምዕራባዉያን ስትወድቁ ዝም ብለዋችኋል፤ አሁን ደግሞ ቱርክ ምን ማድረግ እንደሚቻል ታሳያችኋለች ብለዋል። ይህች ሃገር እንድታንሰራራ ማድረግ እንችላለን፤ ሙስሊም በመሆናች ደግሞ ሶማልያን ከሌላዉ የበለጠ መረዳት እንችላለን ብለዋል። »

በቅርቡ ቱርክ ጦር ሰራዊት ሶማልያ ዉስጥ የሶማልያ መንግሥት ወታደሮች የሚሰለጥኑበት አንድ ጦር ሰፈርን በገንብቶአል።

በቱርክ የሚገኝ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ኤርዶኻን በቱርክና በሌሎች ሃገሮች የከሰስዋቸዉን ሰዎች ችሎት ሲመለከት ኤርዶኻን ሩዋንዳን በመጎብኘት በፕሬዚዳንትነት ስልጣን ለረጅም ዘመን መንበሩን ተቆናጠዉ ለሚገኙት ለዩጋንዳዉ ፕሬዚዳንት ያለምንም ሃፍረት ሥለ- ኃሳብ በነፃነት መናገር እንዲሁም ሥለ ሰብዓዊ መብት ይዞታ ዩዌሪ ሙሴቪኒን አነጋግረዋቸዋል። በኢስታንቡል የሃይንሪሽ ቦል ድርጅት ተጠሪ ክርስቲን ብራክል ቱርክ በአፍሪቃ የንግድ ሸቀጥን ለማስገባት ምንም ዓይነት ፍላጎት የላትም። ስለዚህም ኬንያዉ ፕሬዚዳንት ኬንያታም ሆኑ የዩጋንዳዉ ፕሬዚዳንት ሙሴቪኒ ፤ የቱርኩ ፕሬዚዳንት ትችት ያቀርባሉ ብለዉ ስጋት ሊያድርባቸዉ አይገባም።

« ቱርክ ትልልቅ ገቢ የሚያስገኙ የንግድ ቁሳቁስዎችዋን ለመላክ፤ በአዎንታዊም ሆነ በአሉታዊ ኃሳብ ምንም አይነት ፍላጎት የላትም። እንደኔ እምነት ኤርዶኻን የፕሬስ ነፃነት ይዞታችሁ በጣም ሰፊ ነዉ ቢሉ እንኳ ሙሴቪኒ ኤርዶኻን በሚናገሩት መፍራት የለባቸዉም ብዬ አምናለሁ። ኤርዶዋን የፕሬስ ይዞታችሁ የማኅበረሰቡ ነፃነት ትንሽ ለቀቅ ማለት አለበት ብለዉም አይናገሩም »

አንቶኒዮ ካሽካይሽ / አዜብ ታደሰ
አርያም ተክሌ

Erdogan in Somalia
የቱርኩ ፕሬዚዳንት ሬቼብ ጠይብ ኤርዶኻን ሶማልያን በበጎርጎረሳዉያኑ 2011ዓ,ም በጎበኙበት ወቅትምስል picture-alliance/dpa
Uganda Kampala Yoweri Museveni und Erdogan
ምስል picture-alliance/AA/K. Ozer
ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ