1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቲለርሰን ጉብኝት በአዲስ አበባ

ሐሙስ፣ የካቲት 29 2010

የአፍሪቃ ጉብኝታቸዉን በኢትዮጵያ የጀመሩት የአሜሪካን የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቲለርሰን ዛሬ አዲስ አበባ ላይ ጋዜጣዊ መግለጫዎችን ሰጡ። ቲለርሰን ከአፍሪቃ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ጋር በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የአፍሪቃ ሃገራት የገንዘብ ድጋፍ ከሚያደርጉላቸዉ ሃገራት በኩል ያለዉን አካሄድ እንዲያስተዉሉ አሳስበዋል።

https://p.dw.com/p/2tyUr
Äthiopien Rex Tillerson und Moussa Faki Kommissionsvorsitzender Afrikanische Union (AU)
ምስል Getty Images/AFP/S. Maina

በሀገሪቱ የበለጠ ነፃነት እንዲኖር ጥሪ አቅርበዋል፤

የአፍሪቃ ሃገራት ጉብኝታቸዉን በኢትዮጵያ የጀመሩት የዩናይትድ ስቴትስ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቲለርሰን በዛሬዉ እለት አዲስ አበባ ላይ ጋዜጣዊ መግለጫዎችን ሰጡ። ቲለርሰን ቀደም ብለዉ በአፍሪቃ ኅብረት ተገኝተዉ ከኅብረቱ ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ጋር በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የአፍሪቃ ሃገራት የገንዘብ ድጋፍ ከሚያደርጉላቸዉ ሃገራት በኩል ያለዉን አካሄድ እንዲያስተዉሉ አሳስበዋል። ቻይና ለአፍሪቃ ሃገራት በችግራቸዉ ወቅት የገንዘብ ድጋፍ ብታደርግም በሥራ ፈጠራዉም ሆነ በስለጠናዉ ረገድ እንደማትራዳ ዋሽንግተን እየተመለከተች መሆኗንም ጠቁመዋል። የአሜሪካዉ ፕሬዝደንት ከወራት በፊት በአፍሪቃ ሃገራት ላይ የሰነዘሩት ጽርፈት ያለፈ ጉዳይ መሆኑን ያመለከቱት ሙሳ ፋኪ በበኩላቸዉ የቲለርሰን ጉብኝት አፍሪቃ እና አሜሪካ ላላቸዉ ግንኙነት ዋና ማሳያ ነዉ ብለዋል። ጌታቸዉ ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።

ጌታቸዉ ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ

ሸዋዬ ለገሠ