የታራሚዎች ቤተሰቦች ጥያቄ
ረቡዕ፣ ጳጉሜን 2 2008ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ መንግስት 23 ታራሚዎች በጥይት ተመተው እና በእሳት ተቃጥለው መሞታቸውን ቢያረጋግጥም ማንነታቸው እስካሁን አላሳወቀም። የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ግን በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የሞቱ ሰዎች ቁጥር መንግስት ከገለፀው በላይ ሳይሆን አይቀርም ሲሉ ይደመጣል። በእሳት ቃጠሎው የሞቱ ሰዎች ማንነት ለማወቅ ዛሬ ወደ ማረሚያ ቤቱ ያቀኑ የታራሚዎች ቤተሰቦች በጸጥታ ኃይሎች ተበትነዋል።
ዮሐንስ ገብረእግዚዓብሔር
እሸቴ በቀለ
ነጋሽ መሐመድ