1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የታሰሩት የድረገጽ ጸሐፍት የፍርድ ቤት ውሎ

ረቡዕ፣ ሚያዝያ 29 2006

የኢትዮጵያ ፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የአራዳ ምድብ ችሎት ፣ ፖሊስ ከ10 ቀናት በፊት በታሰሩት በ6 ድረገጽ ጸሐፍት ጉዳይ ላይ ዛሬ የጠየቀውን የ15 ቀናት የምርመራ ጊዜ ወደ 10 ቀናት ዝቅ አደርጓል።

https://p.dw.com/p/1BvLV
Symbolbild Justitia Justizia
ምስል Imago

ከሰዓት በኋላ በዝግ በተካሄደው ችሎት ተከሳሾቹ ለመጀመሪያ ጊዜ ፍርድ ቤት ሲቀርቡ ከውጭ ኃይሎች ጋር በመተባበር ማህበራዊ ሚዲያዎችን በመጠቀም ትርምስ ለመፍጠር አሲረዋል ተብለው የተመሰረተባቸው ክስ ዛሬ ከሽብርተኝነት ጋር ተያይዞ መቅረቡን የተከሳሾቹ ጠበቃ ለዶቼቬለ አስታውቀዋል። በዚህ የተነሳም የዋስ መብት እንደተነፈጋቸው ጠበቃቸው ተናግረዋል።

የአዲስ አበባው ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚዘብሔር አጭር ዘገባ ልኮልናል። በተያያዘ የፍርድ ቤት ዜናም፤ የኢትዮጵያ ፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 11ኛ ይግባኝ ሰሚ ፍትሃ ብሄር ችሎት ለአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የአመራር አባል ለአቶ አስራት ጣሴ ይግባኝ ብይን ለመስጠት ዛሬ ሌላ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጠ ። ፍርድ ቤቱ ዛሬ ለአቶ አስራት ይግባኝ ውሳኔ ይሰጣል ተብሎ ነበር ። ሆኖም ዳኛው ምርመራውን አላጠናቀቅኩም ሲሉ ውሳኔ ለመሰጠት ለግንቦት 19 2006 ዓም ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠታቸውን የአዲስ አባባው ወኪላችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ዘግቧል።

ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር

ሸዋዬ ለገሠ

ሂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ