1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የታቸር ቀብር

ረቡዕ፣ ሚያዝያ 9 2005

ብሪታንያ ዉስጥ ከቀድሞዋ የሐገሪቱ ልዕት ዳያና የቀብር ሥነ-ሥርዓት ወዲሕ በርካታ ሕዝብ ለሥንብት ሲወጣ የዛሬዉ የመጀሪያዉ ነዉ።ይሁንና ታቸርን የሚቃወሙ ሰዎችም አስከሬኑ ለሥንብት በተቀመጥበት አካባቢ ተሰልፈዉ ሟቿን ፖለቲከኛ ሲያወግዙ ነበር።

https://p.dw.com/p/18HSi
The coffin of former British prime minister Margaret Thatcher, draped in the Union Flag, is carried on a gun carriage drawn by the King's Troop Royal Artillery during her funeral procession in London April 17, 2013. Thatcher, who was Conservative prime minister between 1979 and 1990, died on April 8 at the age of 87. Reuters/Matt Dunham/Pool (BRITAIN - Tags: POLITICS OBITUARY SOCIETY MILITARY TPX IMAGES OF THE DAY)
ምስል Reuters



ባለፈዉ ሳምንት ያረፉት የቀድሞዋ የብሪታንያ ጠቅላይ ሚንስትር ማርጋሬት ታቸር ዛሬ ተቀበሩ። በሥንብቱ ሥነ-ሥርዓት ላይ የብሪታንያዋን ንግሥት ጨምሮ የአንድ መቶ ሰባ ሐገራት መሪዎች፥ ሚንስትሮች፥ ባለሥልጣናትና በብዙ ሺሕ የሚቆጠር የብሪታንያ ሕዝብ ተገኝቷል።ብሪታንያ ዉስጥ ከቀድሞዋ የሐገሪቱ ልዕት ዳያና የቀብር ሥነ-ሥርዓት ወዲሕ በርካታ ሕዝብ ለሥንብት ሲወጣ የዛሬዉ የመጀሪያዉ ነዉ።ይሁንና ታቸርን የሚቃወሙ ሰዎችም አስከሬኑ ለሥንብት በተቀመጥበት አካባቢ ተሰልፈዉ ሟቿን ፖለቲከኛ ሲያወግዙ ነበር።የሥንብትና የቀብር ሥነ-ሥርዓቱ እንዳይታጎል የብሪታን ፀጥታ አስከባሪዎች የለደን ከተማ በጥብቅ ሲቆጣጠሩ ነዉ የዋሉት።ታቸር በኑዛዛቸዉ መሠረት አስከሬናቸዉ ተቃጥሎ አመዱ ነዉ-የሚቀበረዉ።የለንደኑ ወኪላችን ድልነሳ ጌታነሕን በሥልክ አነጋግሬዋለሁ።

ድልነሳ ጌታነህ

ነጋሽ መሐመድ

ሂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ