1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የታዳሽ ኃይል ፍላጎት ሊጨምር መቻሉ

ረቡዕ፣ ኅዳር 15 2008

የዓለም ቀፍ የታዳሽ ኃይል ተቋም « IRENA » የዓለም የታዳሽ ኃይል ፍላጎት በ2030 በሁለት እጥፍ እንደሚጨምር በቅርቡ ይፋ ባደረገዉ ጥናት አሳይቷል። በዚህም የተነሳ፣ በአካባቢዉ ያሉ ባለሙያዎች አፋጣኝ የኃይል ለዉጥ እንደሚደረግ መንግስታትን እየመከሩ ይገኛሉ።

https://p.dw.com/p/1HCe4
Solarsiedlung in Freiburg
ምስል picture-alliance/dpa

የታዳሽ ኃይል ፍላጎት ሊጨምር መቻሉ

ታዳሽ ኃይል ምንጮች የሥራ እድሎችንለመፍጠርም ሆነ የአከባቢ ብክለትን ለመቀነስ ትልቅ ሚና እንደሚጫወቱባለሙያዎች ይናገራሉም። የዓለም አቀፍ የታዳሽ ኃይል ተቋም « IRENA» 82 የታዳሽ ኃይል ባለሙያዎችን ይዞ ለ42 ሀገሮች የኃይል አጠቃቀማቸዉንወደታዳሽ ኃይል እንዴት መቀየር እንደሚችሉእና ሌሎች ተጨማሪ አስፈላጊና ጠቃሚ ምክሮችን ለመለገስ ተዘጋጅቷል።

ባለሙያዎቹ የተለያዩ የታዳሽ ኃይል ምንጮችን፤ ወጪዎቻቸዉን፣ የሰዉ ኃይል ገበያ ላይ ሊኖር የሚችለዉን ተፅዕኖ፣ ብክለትን ለመቀነስ የሚጫወተውን ሚና፣ ከዛም አልፎ በመንግስትወይም ህብረተሰብ ግብይት ላይ ሊያመጣ የሚችለዉን ጥቅምና ጉዳት አጥንተዋል።

መርጋ ዮናስ

አዜብ ታደሰ