1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የትራምፕ ትዕዛዝ እና የሶማሌ ማህበረሰብ 

ረቡዕ፣ ጥር 24 2009

ትዕዛዙ ከተላለፈ በኋላ ደግሞ የአሜሪካን ቋሚ የሥራ እና የመኖሪያ ፈቃድ ያላቸው ሶማሊያውያን ለጉዞ በተለያዩ አውሮፕላን ጣቢያዎች በተገኙበት ወቅት መታሰራቸው እና መንገላታታቸውን ሶማሊያውያን ይናገራሉ ።

https://p.dw.com/p/2Wmio
Präsident Trump unterschreibt Dekret im Oval Office Weißes Haus
ምስል picture-alliance/CNP/A. Harrer

Beri Wash.(Ethio-Somali- Americans Rx on Trump's Anti Immigration order) - MP3-Stereo

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ካፀደቁት በኋላ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ተግባራዊ መሆን የጀመረው  የጉዞ እገዳ  ሰለባ ከሆኑት መካከል በአሜሪካን የሶማሌ ማህበረሰብ አባላት ይገኙበታል ። ትራምፕ  እገዳውን ከመፈረማቸው ከሁለት ቀናት በፊት 90 ሶማሌዎች ከአሜሪካን እንዲባረሩ ተደርጓል ። ትዕዛዙ ከተላለፈ በኋላ ደግሞ የአሜሪካን ቋሚ የሥራ እና የመኖሪያ ፈቃድ ያላቸው ሶማሊያውያን ለጉዞ በተለያዩ አውሮፕላን ጣቢያዎች በተገኙበት ወቅት መታሰራቸው እና መንገላታታቸውን ሶማሊያውያን ይናገራሉ ። ከትራምፕ ትዕዛዝ በኋላ በመወሰድ ላይ ባሉት በነዚህ እርምጃዎች አሜሪካ የሚኖሩ የሶማሌ ማህበረሰብ  አባላት በፍርሃት መዋጣቸዉን የዋሽንግተን ዲሲው ወኪላችን መክብብ ሸዋ ዘግቧል ። 
መክብብ ሸዋ 
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ