1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ትራምፕ ከዚህ ቀደም አብዝተው ባብጠለጠሉት የተ.መ.ድ. የመጀመሪያ ንግግራቸውን አድርገዋል

ማክሰኞ፣ መስከረም 9 2010

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ከተገደዱ 26 ሚሊዮን ዜጎች ያሏትን ሰሜን ኮሪያ ድምጥማጧን እንደሚያጠፉ ዛቱ። የፕሬዝዳንቱ ንግግር ቀድሞውኑ ለከረረው ውጥረት ማባባሻ እንዳይሆን አስግቷል። አገራቸው ታላቅ ትዕግስት እና ኃይል እንዳላት የተናገሩት ትራምፕ በሰሜን ኮሪያው መሪ ላይም ተሳልቀዋል።

https://p.dw.com/p/2kJQB
UN Generalversammlung in New York | Donald Trump, Präsident USA
ምስል Getty Images/S. Platt

የትራምፕ ንግግር


የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ስለ ተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሚሰጧቸው አስተያየቶች ሁል ጊዜም አወዛጋቢ ናቸው። በጎርጎሮሳዊው 2005 ዓ.ም. "እኔ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አድናቂ ነኝ" ያሉት ሰው ባለፈው ዓመት «ድርጅቱ ደካማ ነው» ሲሉ ወቅሰውታል። በምረጡኝ ዘመቻቸው ወቅት ድርጅቱ የተዋጣለት ሥምምነት መፈጸም አልቻለም ሲሉ ነበር። "የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ለችግር መፍትሔ ሲያበጅ አይታችሁ የምታውቁት መቼ ነው? መፍትሔ መፍጠር አይችልም" ብለውትም ያውቃሉ። ባስ ሲልም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የዴሞክራሲ ወዳጅ አይደለም እስከ ማለት ደርሰዋል። እኚሁ ሰው ታዲያ አብዝተው ሲያብጠለጥሉት ከከረሙት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ፊት ቀርበው ዛሬ ንግግር አድርገዋል።  ወደ ስቱዲዮ ከመግባቴ በፊት ስለ ንግግራቸው ዋሽንግተን የሚገኘውን የዶይቼ ቬለ ወኪል መክብብ ሸዋን አነጋግሬዋለሁ። 

መክብብ ሸዋ

እሸቴ በቀለ

ነጋሽ መሐመድ