1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የትራምፕ ዉሳኔ እና የበካይ ጋዞች ቅነሳ

ማክሰኞ፣ ግንቦት 29 2009

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ እንደተገመተዉ ሀገራቸዉ ከባቢ አየር በካይ ጋዞችን ለመቀነስ ሃገራት ከተስማሙበት የፓሪሱ የአየር ንብረት ስምምነት እንደምትወጣ አሳዉቀዋል።

https://p.dw.com/p/2eCe3
USA Proteste gegen Trumps Rucktritt vom Pariser Abkommen
ምስል Picture alliance/AP Images/S. Walsh

የትራምፕ ዉሳኔ እና የበካይ ጋዞች ቅነሳ

ለዓለማችን ከባቢ አየር ብክለት በግንባር ቀደምትነት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ከሚያደርጉት አንዷ የሆነችዉ ዩናይትድ ስቴትስ ከዚህ ዉል መዉጣቷን ይፋ ብታደርግም ሌሎች በርካታ ሃገራት ግን በዉላቸዉ እንደሚፀኑ እየገለጹ ነዉ። ዋሽንግተን በጎርጎሪዮሳዊዉ 1997 ዓ,ም ከተፈረመዉ ከታሪካዊዉ የኪዮቶ ስምምነት አንስቶ የአየር ንብረት ለዉጥን ለመግታት በሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ዉስጥ ከቀሪዉ የዓለም ሃገራት ጋር ተባብራ ላለመሳተፍ ምክንያቶችን እየደረደረች ራሷን ስታገልል ታይቷል። 84 ሃገራት የኪዮቶን ዉል ፈርመዋል። አስገዳጅ የነበረዉ የኪዮቶ ዉል የጊዜ ገደቡ ሲያበቃ የሙቀት አማቂ ጋዞችን ልቀት በመቆጣጠር የአየር ንብረት ለዉጥን ለመግታት ይረዳል ተብሎ የታሰበዉን የፓሪስ ስምምነት የተቀበለችዉ ዩናይትድ ስቴትስ በአዲሱ ፕሬዝደንቷ «የአየር ንብረት ለዉጥ የሚል ነገር የለም» በሚል አቋም ምክንያት ዳግም ከሌላዉ ዓለም የተለየ መንገድ ጀምራለች።  የዋሽንግተን ዉሳኔ  ምን ያስከትላል፤ ተግባራዊነቱስ እንዴት ነዉ? የዩናይትድ ስቴትስ ብዙ ከተደከመለት የፓርስ የአየር ንብረት ስምምነት መዉጣት እንደኢትዮጵያ ላሉ ሃገራት ምን ማለት ይሆን? የሚሉትንና ሌሎች ተያያዥ ጥያቄዎች በማስናት በካናዳ ካልጋሪ ዩኒቨርሲቲ የአካባቢ ተፈጥሮ ዲዛይን ፋኩልቲ ተባባሪ ፕሮፌሰር እና የዘርፉ ተመራማሪ፤ ለሆኑት ዶክተር ጌታቸዉ አሰፋ፤ እንዲሁም በኢትዮጵያ የደንና የአካባቢ ጥበቃ ሚንስቴር የአየር ንብረት ለዉጥ ትግበራ ዳይሬክተር ጄኔራል አቶ ደባሱ ባይየለኝን አነጋግረናል። የመጀመሪያዉን ክፍል ከድምጽ ዘገባዉ ያድምጡ።

Trump, Paris Abkommen, Climate Change, Karikatur, Elkin, Sergey Elkin

ሸዋዬ ለገሠ

አዜብ ታደሰ