1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የትራፊክ መጨናነቅ በኬንያ

ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 18 2009

በመንገድ ትራፊክ መጨናነቅ የሚባክን ጊዜ የለም ይላል «ማ ስሪ ሩት» የናይሮቢዉ የጉዞ መረጃ ድረ-ገጽ። የድረ-ገጹ ምክትል ሥራ አስኪያጅ ስቴፋን ኢቦኮ እንደሚናገሩት ድረ-ገጹ ለአሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን በማመላከት የትራፊክ ፍሰትን ጤናማ ለማድረግ እየጣረ ነዉ።

https://p.dw.com/p/2UvmL
Nairobi Straßen Verkehr
ምስል AP

[No title]


በኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ መንገዶችና አውራ ጎዳናወች ላይ ከፍተኛዉን የትራፊክ መጨናነቅ ተቋቁሞ መጓዝ ለእግረኛም ሆነ ለአሽከርካሪ ፈታኝ ነዉ። ለ300 ሺህ  ሰዎች ታስበዉ የተሰሩ መንገዶች አሁን  4 ሚሊዮን  ለደረሰዉ  የከተማዋ ነዋሪ አገልግሎት እየሰጡ ነዉ። በአነዚህ  በተራፊክ በተጨናነቁ መንገዶች አዘዉትረዉ  የሚመላለሱት የናይሮቢ ነዋሪ ስቴፋን ኢቦኮ  የሚያጋጥማቸዉን የዕለት- ተዕለት ችግር  እንዲህ ይገልጹታል።
እንደማስበዉ እያንዳንዱ ሰዉ ከትራፊክ መጨናነቅ ጋር ጉዳዮችን ማያያዝ ይችላል።ትራፊክ መጨናነቅ ዉስጥ በምትገባበ ጊዜ ለምን በየቀኑ በትራፊክ መጨናነቅ ሳታትን እንደምታሳልፍ በእርግጠኝነት ምክንያቱን አታዉቅም። ። በጣም ሊያሳስብህ ይችላል።በእርግጥ ያስጨንቅሃል፤ ግዜንም ያባክናል።
  የ 34 ዓመቱ ነጋዴ እስቴፋኒ የ ኢቦኮ ችግሩን በማጤን ይመስላል ለመፍትሄዉ አየሠሩ ነዉ።  አሳቸዉ በሥራ አስኪያጅነት  የሚመሩት  የናይሮቢ  የጉዞ የመረጃ  ድረ ገጽ  በበይነ  መረብና በተንቀሳቃሽ ስልክ የትራፊክ መረጃን ይሰጣል ።  «ማ ስሪ ሩት » የተሰኘዉ ይሄዉ ድረ ገጽ ከተለያዩ  አካባቢዎች በመሰብሰብ  የየዕለቱን  ትኩስ  የትራፊክ መጨናነቅ  መረጃ  ለአሽከርካሪዎች ያደርሳል ተብሏል።
ስቴፋን ኢብኮ እንደሚናገሩት ከአሽከርካሪዎች የሚጠበቀዉ ለጉዞ ከመነሳታቸዉ በፊት ድረ ገጹን  መጎብኝት ብቻ ነዉ። ሥራ የበዛባችዉን መንገዶች  ከነጻዎቹ  ለይቶ ያሳያል።  በመረጃዉ መሠረትም  ተገልጋዩ  አማራጭ መንገዶችን  ይጠቀማል።  ከዚያም ይላሉ ሰቴፋን ኢቦኮ በትራፊክ መጨናነቅ ሳቢያ የሚጠፋ ጊዜ  የሚፈጠር ጭንቀት  የለም።  አጠቃቀሙን ደግሞ  እንዲህ ያበራራሉ።                         
በቀላሉ የምንፋልገዉን መንገድ ስም መጻፍ እንችላለን።እናም ለምንፈልገዉ የተll,የ መንገድ ወቅታዊ አማራጮች ይመጣሉ።በዚህ መንገድ ከመነሳታችን በፊት ጉዟችንን ቀድመን ማቀድ እንችላለን።
ድህረ ገጹን በየቀኑ የሚጎበኙ ሰዎች ቁጥር አሁን 500 ሺህ ደርሷል። እነዚህ ጎብኝዎች መረጃ በመስጠት ረገድም አጋዥ ናቸዉ። የታከሲ አሽከርካሪዉ ጀምስ ሙባይ ከድረ ገጹ ተጠቃሚዎች አንዱ ነዉ። «ኤምኤ ስሪ ሩት» የአሽከርካሪነት ሥራዉን የተቃና እንዳደረገለት ይገልጻል።                                     
ናይሮቢ ሁልጊዜ ከፍተኛ የሆነ የትራፊክ መጨናነቅ ችግር አለ። እናም ጓደኛየ ነዉ«ማ ስሪ ሩት» ን እንድጠቀም ነገረኝ። መተግበሪያዉ የትራፊክ መጨናነቅ ሲኖር ይሰራል።ከትራፊክ መዘጋጋት ለመዉጣትም ረድቶኛል።
«ማ ስሪ ሩት» የናይሮቢ ከተማን ብሎም የኬንያን የትራፊክ ፍሰት ጤናማ ከማድረግ ባሻገር ስለ መንገድ ትራፊክ ደህንነትና ስለ አሽከሪካሪወች ጥንቃቄም መረጃ ይሰጣል። የኬንያ ብሄራዊ የመንገድ ደህንነት ባለስልጣን መሥርያ ቤትም ከዚሁ ድረ ገጽ ጋር በትበበር ይሠራል ። የባለስልጣን መሥሪያ  ቤቱ  ምክትል ዳይሬክተር  ጆን ምሁያ  እንደሚሉት የመሥሪያ ቤታቸዉ የትራፊክ ትምህርት ክፍል የጥንቃቄ መልክቶችን በዚሁ ድረ ገጽ በኩል ለህዝብ እንዲደርስ ያደርጋል።
የናይሮቢዉ ስቴፋን ኢቦኮ ሃሳብ የከተማዋን ነዋሪዎች የዕለት-ተዕለት የህይወት እንቅስቃሴ አቃሏል ተብሏል። ይህ የተሳካ የተባለዉ ሥራቸዉም አዳዲስ ሀሳብ ጨምረዉበት የትራፊክ ፍሰትን ጤናማ ለማድረግ ወደ ሌሎች የአፍሪቃ ትልልቅ ከተሞች እያስፋፉ መሆኑም ተገልጿል።


ፀሐይ ጫኔ 


አዜብ ታደሰ