1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የትንሣኤ በዓል በመላው ዓለም በተመሣሣይ ቀን

ሐሙስ፣ ሚያዝያ 9 2006

ዘንድሮ የትንሣኤ በዓል በመላው ዓለም በሚገኙ ክርስቲያኖች ዘንድ በተመሳሳይ ቀን ይከበራል። የአይሁዳውያን ፋሲካም በትንሣኤ ቀን ይውላል። የትንሣኤ በዓል ከሐይማኖታዊ ዳራው ባሻገር እንደየሀገሩና የእምነቱ ተከታዮች ዘንድ የተለያዩ ባህላዊ እሴቶችም አሉት። በተለይ የዶሮ እንቁላል ሀገር ቤትም ሆነ እዚህ ጀርመን በትንሣኤ በዓል ልዩ ስፍራ ይሰጠዋል።

https://p.dw.com/p/1Bjoj
ምስል dapd

የትንሣኤ በዓል በመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ ክርስቶስ ሞትን ድል አድርጎ የተነሳበት ዕለት ነው። ዕለቱ በክርስትያኖች ዘንድ እጅግ ታላቅ በዓል ተደርጎ ይታያል። የፊታችን እሁድ የሚከበረውን የትንሣኤ በዓል ወይንም የፋሲካ ምንነትን በጀርመን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን የኑረንበርግ ቅ/ሥላሴ አጥቢያ ኃላፊ መሪጌታ ዳዊት ከፍያለው እንዲህ ያብራራሉ።

በብሉይ ዘመን በግብፅ ፈርዖን አገዛዝ የባርነት ዘመን ይገፉ የነበሩ አይሁዳውያን ነፃ ከወጡ በኋላ 40 ዓመታት በበረሃ ሲጓዙ የተለያዩ ሃይማኖታዊ ትውፊቶችን ያከናውኑ ነበር። እነዚያ ትውፊቶች ዛሬም ድረስ በተለያዩ ቦታዎች ይስተዋላሉ። እስራኤል ሀገር ነዋሪ የሆነው ደራሲና ጋዜጠኛ ዜናነህ መኮንን የአይሁዳውያን የፋሲካ በዓል ትርጓሜና ምንነት እንዲህ ይገልጣል።

Israel Jerusalem St Magdalena
ምስል DW/S. Legesse

የትንሣኤ በዓል ከሚውልበት ቀን ቀደም ብሎ ጀምሮ ዘንድሮ ከትንሣኤ በዓልም ጋ የሚገጣጠመው የአይሁድ ፋሲካ ሁለት አይነት አከባበር እንዳለው ወኪላችን ግርማው አሻግሬ ከእዛው ከእስራኤል እንዲህ ያብራራል።

በጀርመን ሀገር እዚህ ቦን ከተማ ውስጥ ኢትዮጵያውያን የፕሬቴስታንት እምነት ተከታዮችን በማስተባበር የሚታወቁት ወ/ሮ ወርቅነሽ ሽሚትስ የትንሣኤ በዓልን ከጀርመናውያን ጋ በአንድነት እንደሚያከብሩ ጠቅሰዋል።

ጀርመን ባቫሪያ ግዛት ውስጥ የሚገኘው የኒደርአልታይሽ ገዳም አበምኔት ዶ/ር ማሪያኑስ የትንሣኤው ምሽት ጥልቅ መሆኑን ይገልፃሉ።

«በፆሙ ወቅትና በፋሲካው የሚደመጠው እጅግ ጥልቅ የሆነ ዝማሬና መወድስ ነው። የትንሣኤ ሌሊት አቋቋም አራት ሠዓታት ይወስዳል። የቅዳሴው አገልግሎት ማለቴ ነው።»

ልጆች ጥንቸሏ በትንሣኤ ወቅት የሚቀርበውን እንቁላል እራሷ ትደብቃለች ብለው ያምናሉ
ልጆች ጥንቸሏ በትንሣኤ ወቅት የሚቀርበውን እንቁላል እራሷ ትደብቃለች ብለው ያምናሉምስል picture-alliance / dpa/dpaweb

ከጥንት ጀምሮ ሲከበር እዚህ የደረሰው የትንሣኤ በዓል በተለያዩ ቦታዎች የተለያዩ ትውፊታዊ አከባበሮች አሉት። ለአብነት ያህል ከአርመንያ፣ ተነስቶ ሩስያ፣ ከእዚያም ግሪክን አሳብሮ የሜዲትራኒያን ባሕርን ተገን አድርገው ወደተቆረቆቱ ሃገራት ደርሶ በኋላ ላይም ወደ መካከለኛው አውሮጳ የተሻገረው በትንሣኤ ወቅት የሚቀርበው እንቁላል ይጠቀሳል። በጀርመንኛ «ኦስተር አይር» ይባላል። የትንሣኤ ጥንቸል፤ ማለትም «ኦስተር ሐዘ» የደበቀችው እንቁላል ለማለት ነው።

በትንሣኤ ወቅት የሚቀርበው እንቁላል ዘመን ተሻግሮ እዚህ ጀርመንም ህፃናት በትንሣኤ ቀን እሁድ የተቀባባ እንቁላል ከተደበቀበት እንዲፈልጉ ይደረጋል። በቦን ከተማ ነዋሪ የሆኑት ወ/ሮ ማኅሌት ካሳሁን፤

በትንሣኤ ወቅት የሚቀርበው እንቁላል ጀርመን ውስጥ መጀመሪያ ይቀቀልና ቀለም ይቀባል። ልጆች ከተደበቀበት ፈልገው ሲያገኙት እንዲበሉ ይደረጋል። ኢትዮጵያ ውስጥም ከጥንት ጀምሮ አቅሙ የፈቀደለት አማኝ በትንሳኤ በዓል ዶሮ ወጥ ሰርቶ የተቀቀሉ እንቁላሎችን ዶሮ ወጡ ውስጥ ከትቶ መመገብ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ ባህል ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ ሌሊት ቅዳሴ ከተጠናቀቀና የትንሣኤ የምስራች ከተነገረ በኋላ ሰዉ እርስ በእርስ መጠያየቁም እራሱን የቻለ ትውፊት እንደሆነ መሪጌታ ዳዊት ከፍያለው ይጠቅሳሉ።

Felsendom Jerusalem
ምስል picture-alliance/Zumapress/S. Qaq

የትንሣኤ እንቁላል ትውፊት ታሪካዊ አመጣጥ ይህ ነው ተብሎ በውል ባይታወቅም ከአይሁዳውያን የፋሲካ በዓል አከባበር ጋ ተያይዞ የመጣ እንደሆነ ይነገራል። አይሁዳውያን በፋሲካ በዓል ዋዜማ ተሰባስበው ባህላዊ ምግብ የመመገብ ልማድ አላቸው። ይህ ባህላዊ ምግብ ከሚያካትታቸው የምግብ አይነቶች መካከል ደግሞ የተቀቀለ እንቁላል ይገኝበታል። ሌሎች ትውፊታዊ ክንውኖችን ዜናነህ መኮንንእንዲህ ያብራራል።

ለማድመጥ ከታች የድምጽ ማጫወቻውን ይጫኑ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ