1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቻይናዉ ፕሬዝደንት በአሜሪካ

ረቡዕ፣ ጥር 11 2003

የቻይናዉ ፕሬዝደንት ሁ ጂንታኦ ለአራት ቀናት ይፋዊ ጉብኝት ዋሽንግተን ገብተዋል።

https://p.dw.com/p/QtZ9
ፕሬዝደንት ኦባማና ፕሬዝደንት ጂንታኦምስል AP

ስኞ ማምሻዉን ወደዩናይትድስቴትስ ያቀኑት የቻይናዉ ፕሬዝደንት በአገሪቱ በሚያኖራቸዉ ቆይታ ከፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ ጋር በሁለቱ ልዕለ ኃያል አገራት መካከል ስለሚኖረዉ የንግድ ግንኙነት፤ በገንዘብና በሰሜን ኮርያ ጉዳዮች ላይ እንደሚነጋገሩ ይጠበቃል። ቻይና የገንዘቧን አቅም በመቀነስ በዓለም ገበያ ምርቶቿ በቅናሽ እንዲሰራጩ መዘየዷ በዶላሯ ዓለምን የምታገበያየዉን አሜሪካን እንዳላስደሰተ ይነገራል። እንዲያም ሆኖ ከቻይና ጋ ያላትን ግንኙነት ከፍጥጫ ይልቅ በመግባባት ለማስተካከል መጣሯን የሁለቱ አገራት ፕሬዝደንቶች ፊትለፊት ደጋግመዉ መገናኘታቸዉ እንደሚያመለክት ተንታኞች ይናገራሉ።

አበበ ፈለቀ ፣ ሽዋዬ ለገሰ

ሒሩት መለሰ